Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ 68% የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች እና 51% የሶስተኛ ክፍል ተማሪዎች ማንበብ እንደማይችሉ | TIKVAH-MAGAZINE

በኢትዮጵያ 68% የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች እና 51% የሶስተኛ ክፍል ተማሪዎች ማንበብ እንደማይችሉ ተነገረ

በኢትዮጲያ በተለያዩ የአንደኛ ደረጃ 168 ትምህርትቤቶች በሚገኙ በ 9,000 ተማሪዎች በተጠናዉ ጥናት መሰረት 2ኛ ክፍል ተማሪዎች 68% እና 3ኛ ክፍል ተማሪዎች 51% ያህሉ ማንበብና መጻፍ እንደማይችሉ ተገልጿል።

የተማሪዎችን የትምህርት ዉጤት ለማሻሻል የትምህርት ስርአቱ የተናበበ እና የተቀናጀ ትግበራ አስፈላጊ እንደሆነ በጥናቱ ላይ የተመላከተ ሲሆን የትምህርት ስርአቱ ትኩረት ተሰቶበት ሊሰራ እንደሚገባም ተጠቁሟል።

በተጨማሪም በቅድመ መደበኛ ተማሪዎች ላይ እና ከ 1- 4 ተማሪዎች መሰረታዊ ክሎት ማለትም ማንበብ እና መፃፍ፣ ሂሳብ ማስላት እና የተረጋጋ ስነልቦና እና መልካም ማህበራዊ መስተጋብር እንዲኖራቸው መሰራት አለበት ተብሏል፡፡

በዛሬው እለት ''Rise Ethiopia'' ፕሮግራም በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ አዘጋጅነት በ ሂልተን ሆቴል አየተካሄደ ሲሆን መሰል ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት በ ትምህርት ዙርያ ያሉ ችግሮችን መቅረፍ እንደሚቻል በፕሮግራሙ ላይ መገለጹን ከዩንቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@tikvahethmagazine