Get Mystery Box with random crypto!

#ንብኢንተርናሽናልባንክ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በ2021/22 የበጀት ዓመት 1.76 ቢሊዮን ብር | TIKVAH-MAGAZINE

#ንብኢንተርናሽናልባንክ

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በ2021/22 የበጀት ዓመት 1.76 ቢሊዮን ብር ትርፍ አስመዝግቧል። ይህም የትርፍ መጠን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 139.3 ሚሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው ተገልጿል።

ከእዚህ በተጨማሪ በአሁን ሰዓት የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 61.49 ቢሊዮን ብር መድረሱ የተጠቆመ ሲሆን ይህ የሀብት መጠን ባለፈው በጀት ዓመት ከተመዘገበው የሀብት መጠን 7.3 ቢሊዮን ወይም 13.45 ጭማሪ ማሳየቱ ተጠቁሟል።

ከ23 ዓመታት በፊት በ7 መቶ 17  መስራች አባላት የተቋቋመው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማህበር በአሁን ሰዓት 7578 ሰራተኞችን ይዞ በ410 ቅርንጫፎች በመላ ሀገሪቱ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተነግሯል።

@tikvahethmagazine