Get Mystery Box with random crypto!

በ58 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የዳቦ ፋብሪካ ተመረቀ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ድጋፍ በ | TIKVAH-MAGAZINE

በ58 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የዳቦ ፋብሪካ ተመረቀ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ድጋፍ በግል ባለሃብት የተገነባው ከረዩ ዳቦ ፋብሪካ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡

ፋብሪካው አሁን ላይ በቀን 250 ሺህ ዳቦ በማምረት ስራውን የጀመረ ሲሆን÷ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ በቀን 1 ሚሊየን ዳቦ ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል ።

ለከረዩ ዳቦ ማምረቻ እና ማከፋፈያ መንግስት  የዱቄት  አቅርቦት ስራ  የሚሰራ መሆኑ  የተነገረ ሲሆን የንግድ ቢሮ በሚያወጣው ቅናሽ የዳቦ መሸጫ ተመን እንደሚያከፋፍልም ተገልጿል፡፡

አሁን ላይ ለ30 ሰዎች የስራ ዕድል የፈጠረው ፋብሪካው ÷በቀጣይ 150 የሚጠጉ ሰራተኞች እንደሚኖሩት ከፋና ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@tikvahethmagazine