Get Mystery Box with random crypto!

ከ11 ሺህ በላይ ሰራተኞችን ለመቅጠር በወጣው ማስታወቂያ ከ130 ሺህ በላይ አመልካቾች ለፈተና ቀረ | TIKVAH-MAGAZINE

ከ11 ሺህ በላይ ሰራተኞችን ለመቅጠር በወጣው ማስታወቂያ ከ130 ሺህ በላይ አመልካቾች ለፈተና ቀረቡ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ11 ሺህ በላይ ሰራተኞችን ለመቅጠር ከ130 ሺህ በላይ አመልካቾች የጽሑፍ ፈተና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት ላለፉት አራት ተከታታይ እሑዶች መስጠቱን አስታውቋል።

ፈተናው በአዲስ አበባ የኒቨርሲቲ የንግድ ክፍል የተሰጠ ሲሆን ዩኒቨርስቲው ፈተናውን ከማዘጋጀት ጀምሮ እስከ ውጤት ድረስ በጥንቃቄ ማከናወኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የፈተናውን ሒደት አስመልከቶ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በዛሬው ዕለት በሰጡት የጋራ መግለጫ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ፈተናው ወጥቷል ተብሎ ሲሰራጭ የነበረው መረጃ ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ አንስተዋል። (FBC)

@tikvahethmagazine