Get Mystery Box with random crypto!

የ10 ልጆችና ነብሰጡር የሆነች ባለቤቱን በጥይት መቶ የገደለ ግለሰብ... በደቡብ ክልል ቡርጂ ል | TIKVAH-MAGAZINE

የ10 ልጆችና ነብሰጡር የሆነች ባለቤቱን በጥይት መቶ የገደለ ግለሰብ...

በደቡብ ክልል ቡርጂ ልዩ ወረዳ ነዋሪ የሆነዉ ተጠርጣሪ የ22 ዓመት የትዳር አጋሩና የ10 ልጆች እናት የሆነችዉ ነብሰጡር ባለቤቱን በአንድ ጥይት ደረቷን መቶ የግድያ ወንጀል እንደፈፀመ ከአካባቢዉ ህብረተሰቡ ለፖሊስ በደረሰ ጥቆማ መነሻ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያውለዋል።

ተጠርጣሪዉ በቅርቡ መሬት ሸጦ ክላሽንኮቭ ጠብመንጃ መግዛቱና በተደጋጋሚ ጠጥቶ እየሰከረ ወደቤት መመለሱ ያላስደሰታት ባለቤቱ ድርጊቱን በመቃወሟ ምክንያት ባልና ሚስቱ ይጨቃጨቁ እንደነበር ፖሊስ በአካባቢያዊ ማስረጃ ማረጋገጡ ተነግሯል።

ተጠርጣሪዉ ህዳር 30/2015 ዓ.ም በመጠጥ ሲዝናና አምሽቶ ምሽት 2:00 ሰዓት ላይ ወደ ቤት በመመለስ ከብቶችን ስታግድ የዋለች የትዳር አጋሩን በጥይት ለህልፈት የዳረገበት ምክንያት መሳሪያዉ ባርቆብኝ ነዉ በማለት አስረድቷል።

ይሁን እንጂ ከተጠረጠረበት ወንጀል ለመሸሽ የቀረበ ምክንያት ነዉ ሲል ፖሊስ የግለሰቡን ሀሳብ ዉድቅ የሚያደርግ ተጨባጭ መረጃ እንዳለዉ ገልፆ ወንጀሉ ሆን ብሎ እንደፈፀመዉ አረጋግጫለሁ ማለቱን ደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@tikvahethmagazine