Get Mystery Box with random crypto!

ከጅብሰም ጋር ተጭኖ ወደ ኬኒያ ሊሻገር የነበረ አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ስር ዋለ በደቡብ ክልል ደ | TIKVAH-MAGAZINE

ከጅብሰም ጋር ተጭኖ ወደ ኬኒያ ሊሻገር የነበረ አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ስር ዋለ

በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- አ.አ06344 በሆነ ኤፍኤስአር የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ከጅብሰም ጋር ተቀላቅሎ የተጫነ 6,150 ኪ.ግ ካናቢስ የተሰኘዉ እፅ በቁጥጥር ስር መዋሉ የዞኑ ፖሊስ አስታዉቋል።

አደንዛዥ እጹን የጫነዉ ተሽከርካሪ በኤርቦሬ መስመር በጉዞ ላይ ሳለ በበናፀማይ ወረዳ ወይጦ ወይም ብራይሌ ተብሎ በሚጠራዉ የገጠር ከተማ እንደደረሰ ታህሳስ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ለሊት 8:00 ሰዓት ላይ የደቡብ ልዩ ኃይል አባላት ባደረጉት ክትትል በቁጥጥር ስር መዋሉ ታውቋል።

ሾፌሩ ንብረቱን ከጫነዉ ግለሰብ ጋር ያመለጡ ሲሆን የተሽከርካሪዉ ረዳትና ተሽከርካሪዉን ከነጭነቱ በቁጥጥር ስር አዉሎ ፖሊስ ምርመራ ማጣራት መጀመሩ ታውቋል።

እፁ ከምስራቅ አርሲ ዞን ሻሸመኔ አካባቢ የተጫነ መሆኑን ፖሊስ በምርመራ ማረጋገጡን ከደቡብ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

@tikvahethmagazine