Get Mystery Box with random crypto!

#እንድታውቁት ከኮዬ ፈጬ አደባባይ እስከ ሃጫሉ ሁንዴሳ አደባባይ ያለው መንገድ በውሃ መስመር ዝር | TIKVAH-MAGAZINE

#እንድታውቁት

ከኮዬ ፈጬ አደባባይ እስከ ሃጫሉ ሁንዴሳ አደባባይ ያለው መንገድ በውሃ መስመር ዝርጋታ ምክንያት ከነገ ታህሳስ 5/2015 ዓ.ም ጀምሮ ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ በከፊል የሚዘጋ ይሆናል።

በዚሁ መሰረት በመጀመሪያው ዙሪ ከኮዬ ፈጬ አደባባይ ወደ ሃጫሉ ሁንዴሳ የሚወስደው መንገድ ዝግ ይሆንና በተቃራኒ ያለው መንገድ ወደ ሁለቱም አቅጣጫ አሽከርካሪዎች የሚጠቀሙበት ሲሆን የውሃ መስመር ዝርጋታው ሲጠናቀቅ በተቃራኒው ከሃጫሉ ሁንዴሳ ወደ ኮዬ ፈጬ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ዝግ ሆኖ በተመሳሳይ ሁኔታ የባለአንድ አቅጣጫ መንገዱን ወደ ሁለቱም አቅጣጫ የሚጠቀሙበት ይሆናል።

ስለሆነም የትራፊክ ፍሰቱ እንዳይጨናነቅ እና ደህንነቱም የተረጋገጠ እንዲሆን አሽከርካሪዎች በጥንቃቄ መንገዱን እንድትጠቀሙ፣ በአካባቢው ላይ በስራ ላይ ለሚሆኑ ባለሙያዎች ጥንቃቄ በማድረግና በሚሰጡት አቅጣጫ መሰረት በመንቀሳቀስ የበኩላችሁን ኃላፊነት እንድትወጡ ሲል የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታውቋል።

@tikvahethmagazine