Get Mystery Box with random crypto!

'ኮካ ኮላ በኢትዮጵያ የገንዘብን ሽልማት የሚሸልም ውድድር ወይም ሎተሪ የለውም።' ድርጅቱ ከኮካ | TIKVAH-MAGAZINE

"ኮካ ኮላ በኢትዮጵያ የገንዘብን ሽልማት የሚሸልም ውድድር ወይም ሎተሪ የለውም።" ድርጅቱ

ከኮካ ኮላ የገንዘብ ሽልማት እንዳገኙ በማስመሰል ሰዎች ሽልማቱን ያሸነፉ መሆኑን የሚገልፁ የማጭበርበሪያ መልዕክቶችን በተለያዩ መንገዶች አማካኝነት የሚያሰራጩ ግለሰቦች በመኖራቸው ደንበኞቹ እንዲጠነቀቁ ካንፖኒው በላከልን መልዕክት ገልጾልናል።

"ኮካ ኮላ በኢትዮጵያ የገንዘብን ሽልማት የሚሸልም ውድድር ወይም ሎተሪ የለውም።" ያለው ድርጅቱ ሽልማት የሚያስገኙ ፕሮግራሞች ሲኖሩትም በግልፅ ለህዝብ በማሳወቅና ባሉት የማኅበራዊና የሚዲያ ማስታወቂያዎች እንደሚያስነግር አስታውቋል።

@tikvahethmagazine