Get Mystery Box with random crypto!

ግምታዊ ዋጋው 5 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር የሆነ እርጥብ ጫት በቁጥጥር ስር ዋለ በጅግጅጋ ጉምሩክ | TIKVAH-MAGAZINE

ግምታዊ ዋጋው 5 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር የሆነ እርጥብ ጫት በቁጥጥር ስር ዋለ

በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ህዳር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ግምታዊ ዋጋው 5 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር የሆነ እርጥብ ጫት በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ወደ ጎረቤት ሀገራት በህገወጥ መንገድ ሊወጣ ሲል የተያዘው እርጥብ ጫት፣ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የኢንተለጀንስ ባለሙያዎች እና የኮንትሮባንድ መከላከል ሠራተኞች በጋራ ባደረጉት ጥብቅ ክትትል በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ከጉምሩክ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@tikvahethmagazine