Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር ትራንስፖርት በሩብ ዓመቱ በወጪና ገቢ የጭነት አገልግሎት ከእቅዱ በላይ ማሳካ | TIKVAH-MAGAZINE

የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር ትራንስፖርት በሩብ ዓመቱ በወጪና ገቢ የጭነት አገልግሎት ከእቅዱ በላይ ማሳካቱን አስታወቀ

በበጀት አመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የምግብ ዘይት፣ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ፣የአፈር ማዳበሪያን ጨምሮ የተለያዩ የግብርና ግብዓቶችን ጨምሮ በድምሩ 471 ሺህ ቶን የወጪና ገቢ ጭነት ማጓጓዙ ተጠቅሷል፡፡

በዚህም ከእቅዱ በላይ 104 በመቶ አፈጻጸም ማስመዝገቡን ገልፀው በአገራዊ የወጭና ገቢ ጭነት ሚና ከነበረው የ12 በመቶ ድርሻ ወደ 15 በመቶ ከፍ ማለቱን ተነግሯል፡፡

በባለፈው በጀት ዓመት በቡና ምርት የወጭ ንግድ 98 በመቶ የሚሆነው የተጓጓዘው በኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ከ60 ሚሊዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት እና የአፈር ማዳበሪያን በማጓጓዝ ሎጂስቲክስ አገልግሎት ማሳለጥ ተችሏል የተባለ ሲሆን በዚህም በሎጂስቲክስ 1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር በኢትዮ ጂቡቲ የባቡር ትራንስፖርት በኩል ማግኘቱ ተገልጿል።

የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር በ19 የባቡር ጣቢያዎቹ የወጪና ገቢ ንግድን በማቀላጠፍ በምጣኔ ሃብት እድገት ላይ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ጨምሮ የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

@tikvahethmagazine