Get Mystery Box with random crypto!

የተበደረውን 150 ብር አልመለሰልኝም በማለት አባቱን የገደለው ግለሰብ… በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵ | TIKVAH-MAGAZINE

የተበደረውን 150 ብር አልመለሰልኝም በማለት አባቱን የገደለው ግለሰብ…

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሸኮ ወረዳ ግዠ መሬት ቀበሌ ብርሃን በር ተብሎ በሚጠራበት ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት በዉል ባልታወቀ ሰዓት ወላጅ አባቱን የተበደርከዉ ገንዘብ አልመለስክልኝም በማለት አባቱን በጦር ወግቶ የገደለዉን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።

የግድያዉ መንስኤ ልጅ አባቱን ያበደርኩህን 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) መልስልኝ ብሎ ሲጠይቀዉ አሁን የለኝም ጊዜ ስጠኝ ብሎ በተፈጠረ ፀብ ምክንያት ወንጀሉን መፈፀሙ የተገለጸ ሲሆን ፓሊስ በደረሰው ጥቆማ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ውሎ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

@tikvahethmagazine