Get Mystery Box with random crypto!

በውርስ ከተያዙ ተሽከርካሪዎች ላይ ሰሌዳ እየፈታ ለህገ-ወጥ ተግባር ሲያከራይ የነበረ ግለሰብ ተያዘ | TIKVAH-MAGAZINE

በውርስ ከተያዙ ተሽከርካሪዎች ላይ ሰሌዳ እየፈታ ለህገ-ወጥ ተግባር ሲያከራይ የነበረ ግለሰብ ተያዘ።

የድሬዳዋ ቅርንጫፍ የጉምሩክ የውርስ መጋዘን ፀሀፊ የነበረው በውርስ ከተያዙ ተሽከርካሪዎች ሰሌዳ እየፈታ ለህገ-ወጥ ተግባር ሲገለገልበት እጅ ከፍንጅ መያዙን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገለጸ፡፡

ተጠርጣሪው ወንጀሉን የፈፀመው የድሬዳዋ ቅርንጫፍ የጉምሩክ የውርስ መጋዘን ፀሀፊ ሆኖ እየሰራ ባለበት በሥራ አጋጣሚ በውርስ ከተያዙ ተሽከርካሪዎች ሠሌደ ቁጥር እየፈታ ለደላሎችና በዚህ ህገ-ወጥ ተግባር ላይ ለተሰማሩ ሰዎች በ15 ሺህ ብር ያከራያል።

ሰሌዳውን የሚከራዩት ግለሰቦች ይህንን ሰሌዳ ቁጥር እየተጠቀሙ ከሶማሌ ላንድ ሠነድ አልባ ተሽከርካሪዎችን በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ሲያደርጉ እንደነበር ተገልጿል፡፡

ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር የዋለው 15 ሺህ ብር ተቀብሎ በውርስ ከተያዘ ተሸከርካሪ ሠሌዳ ፈቶ ሲሰጥ በድሬዳዋ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ እጅ ከፈንጅ ተይዞ ፖሊስ ምርመራ እያጣራበት እንደሆነ ከፌደራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

@tikvahethmagazine