Get Mystery Box with random crypto!

አዋሽ-መኢሶ መንገድ ጥገና እየተደረገለት ነው የኢትዮ-ጅቡቲ ዋና መንገድ አካል የሆነው አዋሽ-መኢ | TIKVAH-MAGAZINE

አዋሽ-መኢሶ መንገድ ጥገና እየተደረገለት ነው

የኢትዮ-ጅቡቲ ዋና መንገድ አካል የሆነው አዋሽ-መኢሶ 70 ነጥብ 5 ኪ.ሜ መንገድ የመስመሩን ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት በበቂ ሁኔታ ለማስተናገድ በሚያስችል መልኩ ከባድ ጥገና እየተደረገለት መሆኑ ተነግሯል።

ጥገናውን ሀገር-በቀሉ 'ዮንአብ ኮንስትራክሽን' በ 478,385,156 ብር በሆነ ወጪ በማከናወን ላይ ሲሆን ወጪው ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት እንደሚሸፈን ታውቋል።

የመንገዱ መሠረት እና  ትከሻ ላይ ብልሽት በመስተዋሉ እንዲሁም መንገዱ ከአነስተኛ እስከ ከባድ መጠን ባላቸው ጉድጎዶች(deep holes) እና በሌሎች ነገሮች በመጎዳቱ የጥገና ሥራ እየተከናወነለት ይገኛል ተብሏል።

በእስከ አሁኑ የግንባታ እንቅስቃሴ የ3 ነጥብ 6 ኪ.ሜ የኦቨርሌይ አስፋልት ንጣፍ፣ የተለዋጭ መንገድ እና ሌሎች ሥራዎች  በመከናወን ላይ ሲሆኑ በዚህም ከአጠቃላይ የግንባታ ሥራው 18 በመቶ መከናወኑ ተገልጿል።

መንገዱ የሀገሪቱ የገቢ እና ወጪ ንግድ ዋና መስመር እና ከከባድ እስከ ቀላል ተሽክከርካሪዎች የሚተላለፉበት እንደመሆኑ፥ የአርሶ-አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ይጨምራል ተበሏል።

የዚህ መንገድ ትስስር አካል የሆነው ከአዳማ-አዋሽ (ኪ.ሜ 60) ከባድ ጥገና ፕሮጀክት በግንባታ ላይ የሚገኘ ሲሆን፣ ከመኢሶ- ቁልቢ- ሀረር  ያሉት መንገዶች በጨረታ ሂደት ላይ ናቸው ተብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ የኢትዮ-ጅቡቲ የትራንስፖርት መስመር የሀገሪቱ 90 ከመቶ በላይ የገቢ እና ወጪ ንግድ የሚተላለፍበት እንደመሆኑ ያለውን የትራፊክ ፍሰት ይበልጥ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ሊያስተናግድ የሚያስችል የፍጥነት መንገድ አዳማ-አዋሽ 60 ኪ.ሜ ምዕራፍ አንድ ግንባታ መጀመሩ ይታወቃል፡፡

መረጃው፦የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ነው።

@tikvahethmagazine