Get Mystery Box with random crypto!

'በኢትዮጵያ ላላው ድርቅ ምላሽ ለመስጠት ከጠየቅነው ገንዘብ ውስጥ ያገኘነው 14% ብቻ ነው' - ፋ | TIKVAH-MAGAZINE

"በኢትዮጵያ ላላው ድርቅ ምላሽ ለመስጠት ከጠየቅነው ገንዘብ ውስጥ ያገኘነው 14% ብቻ ነው" - ፋኦ

በኢትዮጵያ በድርቅ በተጠቁ አካባቢዎች የሚገኙ 10 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የተባበሩት መንግስታት የምግብና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) አስታውቋል።

ፋኦ በመግለጫው የሶማሌ፣ ኦሮሚያ፣ ሲዳማ እና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች በከፍተኛ ሁኔታ የተጠቁ አካባቢዎች ናቸው ብሏል።

የሶማሌ ክልልን የጎበኙት የድርጅቱ የአስቸኳይ ግዜ ዕርዳታ ሃላፊ የሆኑት ሬይን ፖልሰን የድርቁን ከፍተኛ አሳሳቢነት አንስተው፣ የተሻለ የአስቸኳይ ግዜ ምላሽ ያስፈልጋል ብለዋል።

ኃላፊው አክለው ለረድኤት ሥራዎች ዋናው ጋሬጣ የሆነው የገንዘብ በበቂ አለመገኘት ሲሆን፣ ፋኦ በኢትዮጵያ ላላው ድርቅ ምላሽ ለመስጠት ከጠየቀው ውስጥ ያገኘው 14 በመቶውን ብቻ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በሶማሌ ክልል ብቻ 691 ሺህ 500 የሚሆኑ ሰዎችን በህይወት አድን ዕርዳታ መታደጉን የገለጸው ድርጅቱ፣ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት በኢትዮጵያ 7.5 ሚሊዮን ሰዎችን መርዳቱን አመልክቷል። (VOA Amharic)

@tikvahethmagazine