Get Mystery Box with random crypto!

የሰው ነብስ አጥፍቶ ለ18 ዓመት ከህግ ተሠውሮ የቆየው ግለሰብ... ጌታወንድፍሬ አበባው የተባለ | TIKVAH-MAGAZINE

የሰው ነብስ አጥፍቶ ለ18 ዓመት ከህግ ተሠውሮ የቆየው ግለሰብ...

ጌታወንድፍሬ አበባው የተባለው ግለሰብ ግንቦት 7/1997 ዓ.ም በመቅደላ ወረዳ ኮሬብ 023 ቀበሌ ላይ ሟች ይብሬ ሙሀመድ የተባለውን ግለሰብ በቂም በቀል ተነሣሥቶ በዱላ በመደብደብና ህይወቱን በማጥፋት ከአካባቢው ተሰውሮ ለ18 ዓመት ከኖረ በኀላ ህዳር 16 ቀን 2015 ዓ.ም በጋምቤላ ክልል ሜጅንግ ዞን ጎደሬ ወረዳ ላይ በቁጥጥር ሥር ውሏል።

የመቅደላ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤትም ፖሊሶችን ወደ ቦታዉ በመላክ ህዳር 26/2015 ዓ.ም ወንጀሉን ወደ ፈፀመበት መቅደላ ወረዳ በማምጣት በቁጥጥር ስር ማድረጉን ከወረዳው ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@tikvahethmagazine