Get Mystery Box with random crypto!

በህገወጥ የማዕድን ዝዉዉር የተጠረጠሩ ግለሰቦችና ቁሳቁሶች በቁጥጥር ስር ዋሉ በደቡብ ምዕራብ ኢት | TIKVAH-MAGAZINE

በህገወጥ የማዕድን ዝዉዉር የተጠረጠሩ ግለሰቦችና ቁሳቁሶች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ምዕራብ ህዝቦች ክልል ኦሞ ዞን ቤሮ ወረዳ በተደረገዉ ድንገተኛ ፍተሻ የተለያዩ ማዕድን ዉጤቶችና መሳሪያዎች መገኘቱ ተገልጿል።

በዚሁ መሠረት 2,260(ሁለት ሺ ሁለት መቶ ስልሳ) ግራም ወርቅ፣ 3 የወርቅ መጠቆሚያ ማሽን ፣2 ክላሽ 1 ሽጉጥ ከ76 መሠል ጥይቶችና 2,129,100(ሁለት ሚሊዬን አንድ መቶ ሀያ ዘጠኝ ሺ አንድ መቶ ብር) በፖሊስ በቁጥጥር ስር ዉሏል።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ 21 ሠዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ በመጣራት ላይ የሚገኝ ሲሆን የህግ ማስከበሩ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@tikvahethmagazine