Get Mystery Box with random crypto!

በኦሮሚያ ክልል የወባ፣ የኩፍኝ  እና የኮሌራ ወረርሽኝ መከሰቱን የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ገለጸ። ወባ፣ | TIKVAH-MAGAZINE

በኦሮሚያ ክልል የወባ፣ የኩፍኝ  እና የኮሌራ ወረርሽኝ መከሰቱን የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ገለጸ።

ወባ፣ ኩፍኝ እና ኮሌራ በሽታዎች በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች በወረርሽኝ መልክ በመከሰታቸው  ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ  የኦሮሚያ ጤና ቢሮ አሳስቧል።

ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የፀረ ወባ  ኬሚካል ርጭት፣ የአጎበር ስርጭት፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች፣ የመድሃኒት አቅርቦትና የፀረ ኮሌራ ክትባት ስራ መካሄዱን የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አበራ ቦቶሬ ለኢብኮ ገልጸዋል።

የተመድ የሠብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (ኦቻ) ሪፖርት መሰረት በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ሦስት ወረዳዎች በሚገኙ 25 ቀበሌዎች እንዲሁም በሶማሌ ክልል በ2 ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ 9 ቀበሌዎች ኮሌራ መከሰቱን ገልጿል።

እስከ ጥቅምት 15 ቀን ባለው መረጃ መሰረት 9 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ እስከ ጥቅምት 21 ድረስ የተጠቂዎች ቁጥር በፍጥነት መጨመሩንና በእነዚህ አከባቢዎች 334 ተጠቂዎች መገኘታቸውንም ሪፖርቱ ያሳያል።

የመጀመሪያው የኮሌራ በሽታ በዚህ ዓመት በባሌ ዞን ነሃሴ 21 መገኘቱን የሚጠቁመው ሪፖርቱ የስደተኛ መጠለያ የሚገኝባቸውን ጨምሮ 114 ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ 459 ሺ ሰዎችም አስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

@tikvahethmagazine