Get Mystery Box with random crypto!

ከሳተላይቶች ጋር በኅብረት የምትሠራ ሌላ ሳተላይት ለማምጠቅ መታቀዱ ተገለጸ ለመሬት ምልከታ የሚያ | TIKVAH-MAGAZINE

ከሳተላይቶች ጋር በኅብረት የምትሠራ ሌላ ሳተላይት ለማምጠቅ መታቀዱ ተገለጸ

ለመሬት ምልከታ የሚያገለግሉ ሳተላይቶችን ካመጠቀ ኩባንያ ጋር ውል በመግባት የኢትዮጵያን ሁለተኛ ሳተላይት አምጥቆ፣ በኅብረ ሳተላይት (satellite constellation) በጋራ መረጃ ለመሰብሰብ ማቀዱን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

ኢንስቲትዩቱ ከሌሎች ሳተላይቶች ጋር በኅብረት የምትሠራ የመሬት ምልከታ ሳተላይት በተያዘው የ2015 በጀት ዓመት ለማምመጠቅ ዕቅድ እንደያዘና ጨረታ ለማውጣትም በዝግጅት ላይ እንደሆነ፣ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ አብዲሳ ይልማ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ሁለተኛዋን ሳተላይት ለማምጠቅ የኢኮኖሚ አዋጭነት ጥናት ሲደረግ መቆየቱን ያስረዱት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ጥናቱ አንድ ሳተላይት ከማምጠቅ ይልቅ በኅብረ ሳተላይት (satellite constellation) ውሰጥ መግባት ተመራጭ እንደሚሆን ማመላከቱን ገልጸዋል፡፡

ኅብረ ሳተላይት ለአንድ ዓላማ ተልከው ምድርን የሚዞሩ ሳተላይቶች ስብስብ ሲሆን፣ ከአንድ የምድር አካባቢ መረጃ ለማግኘት አንድ ሳተላይት ዞሮ እስከሚመለስ ለመጠበቅ ሳያስፈልግ ተተኪ ሆኖ ያንን አካባቢ ከሚዞር ሌላ ሳተላይት መረጃ መቀበል ይቻላል፡፡

ኢትዮጵያ ያላትን 1.1 ሚሊዮን ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት በአንድ ሳተላይት መሸፈን እንደማይቻል፤ "በአዲስ አበባ ላይ አንዴ ብታልፍ መልሳ በአዲስ አበባ ላይ ለማለፍ ሌላ 20 ወይም 30 ቀን ይፈጃል" ሲሉም አስረድተዋል።

ለኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነችው ETRSS-1 የመሬት ምልከታ ሳተላይት የመጠቀችው ከሦስት ዓመት በፊት መምጠቋ ይታወሳል። ሳተላይቷ የተገመተላት የቆይታ ጊዜ ሁለት ዓመት ተኩል ቢሆንም ከታቀደላት ጊዜ 5 ወራትን ጨምራ እስካሁን እያገለገለች ነው ተብሏል፡፡  

[ ሪፖርተር ]

@tikvahethmagazine