Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ ጠዋት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ 1.5 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ | TIKVAH-MAGAZINE

ዛሬ ጠዋት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ 1.5 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር በጨፌ ቀጠና በተለምዶ መስቀልኛ መንገድ አጠገብ ባሉ ሶስት ሱቆች ላይ ነው የእሳት አደጋው የደረሰው ።

አደጋው የተከሰተው ከጠዋቱ 1:30 አካባቢ ሲሆን በአደጋው 1.5 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት የወደመ ሲሆን አንድ የህንጻ መሳሪያ መሸጫ ሱቅ ሙሉ በሙሉ ሲወድም ሁለት የንግድ ሱቆች በከፊል ተጎድተዋል።

አደጋዉን ለመቆጣጠር አንድ ሰዓት  የፈጀ ሲሆን እሳቱ ተዛምቶ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ በማድረግ 10 ሚሊየን ብር የተገመተ ንብረት ማዳን ሲቻል በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩንና መንስኤዉ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ የብስራት ሬድዮ ዘገባ ያሳያል።

@tikvahethmagazine