Get Mystery Box with random crypto!

#AddisAbaba በአዲስ አበባ የኤች አይቪ የስርጭት መጠን 3 ከመቶ መድረሱ ተገልጿል። ነአዲ | TIKVAH-MAGAZINE

#AddisAbaba

በአዲስ አበባ የኤች አይቪ የስርጭት መጠን 3 ከመቶ መድረሱ ተገልጿል። ነአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና የከተማው ጤና ቢሮ በጋራ ባስጠኑት ጥናት በመዲናዋ 48 ወረዳዎች ላይ የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ ከሆነባቸው ክፍለ ከተሞች መካከል አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በቀዳሚነት የተቀመጠ ሲሆን፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ አራዳ እንዲሁም ቦሌ ክፍለ  ከተሞች ላይ ስርጭቱ እያየለ ይገኛል ሲል ጤና ቢሮው አስታውቋል፡፡

ሴተኛ አዳሪዎች በከተማዋ መበራከታቸው ለስርጭቱ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚወስድ የተነገረ ሲሆን በሴተኛ አዳሪዎች የስርጭት መጠኑ 23 ከመቶ እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡ ከሴተኛ አዳሪዎች በተጨማሪም የህግ ታራሚዎች 4 ከመቶ የስርጭት መጠን እንደሚሸፍኑ ተነግሯል፡፡

ዘገባው የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ነው

@tikvahethmagazine