Get Mystery Box with random crypto!

የገንዘብ ሚኒስቴር የኢትዮቴሌኮም ከፊል ሽያጭ ሂደትን በድጋሚ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ፡፡ የኢትዮ | TIKVAH-MAGAZINE

የገንዘብ ሚኒስቴር የኢትዮቴሌኮም ከፊል ሽያጭ ሂደትን በድጋሚ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ፡፡

የኢትዮቴሌኮምን 40 በመቶ ድርሻ ለመሸጥ ዓለም አቀፍ ጨረታ ከዛሬ ጀምሮ እንደሚወጣ የገንዘብ ሚንስቴር አስታወቀ።

መንግስት የኢትዮቴሌኮምን 40 በመቶ ድርሻ ወደ ግል ለማዛወር አውጥቶት የነበረው ዓለም አቀፍ ጨረታ በአለም አቀፍ የኢኮኖሚ መቀዛቀዝና በአገር አቀፍ ደረጃም ምቹ ሁኔታ ስላልነበረ መቋረጡን ተነገሯል።

ዓለም አቀፍ ኩባንያን ለማስገባት ከዛሬ ጀምሮ ጨረታው ለቀጣይ ሶስት ሳምንታት እስከ ዲሴምበር 19 ቀን 2022 ክፍት ተደርጓል።

አሁን በተፈጠረው ስምምነት መሰረትና አለም አቀፋዊ ሁኔታውን ግምት ውስጥ በማስገባት ከሳፋሪኮም ቀጥሎ አንድ ተጨማሪ ኩባንያ ለማስገባት ጨረታ መውጣቱም የተገለጸ ሲሆን ለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣይ አራት ሳምንታት ውይይት እንደሚኖር ታውቋል፡፡ (EPA, Captal)

@tikvahethmagazine