Get Mystery Box with random crypto!

ልማት ባንክ የሶስተኛ ደረጃ ህክምና ለሚሰጡ የጤና ተቋማት ብድር መስጠት ሊጀምር ነው የኢትዮጵያ | TIKVAH-MAGAZINE

ልማት ባንክ የሶስተኛ ደረጃ ህክምና ለሚሰጡ የጤና ተቋማት ብድር መስጠት ሊጀምር ነው

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁና በውጭ አገራት የሚሰጡ የሶስተኛ ደረጃ የህክምና አገልግሎቶችን በሀገር ውስጥ መስጠት ለሚችሉ የጤና ተቋማት ብድር መስጠት ሊጀምር መሆኑን አስታውቋል።

ሶስተኛ ደረጃ (ተርሸሪ ሌቭል) ሆስፒታል ዘመናዊ መሳሪያዎችን አካቶ የተሟላ አገልግሎትን ለታካሚዎች የሚሰጥ ሲሆን ከሁለተኛና አንደኛ ደረጃ ሆስፒታሎች በሪፈር የሚላኩ ታካሚዎችን ተቀብሎ አገልግሎት የሚሰጥ ጤና ተቋም ነው።

የባንኩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው ለኢዜአ እንደተናገሩት በአሁኑ ወቅት ባንኩ ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቁና በውጭ የሚደረጉ የህክምና አገልግሎቶችን በሀገር ውስጥ እንዲጀመር ለማስቻል አገልግሎቱን የሚሰጡ ተቋማትን ለመደገፍ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

በዘርፉ ድጋፍ ለማግኘት ጥያቄ ያቀረቡ መኖራቸውን የገለጹት ፕሬዝዳንቱ ፕሮጀክቱን በቀጣዮቹ አራት ወራት ለማፅደቅ መታቀዱን አስረድተዋል።

@tikvahethmagazine