Get Mystery Box with random crypto!

ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የተገነባው የዓሊ ከተማ-ዋቤ ድልድይና ኮንክሪት አስፋልት መንገድ በፌደራ | TIKVAH-MAGAZINE

ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የተገነባው የዓሊ ከተማ-ዋቤ ድልድይና ኮንክሪት አስፋልት መንገድ

በፌደራል መንግስት የተገነባውና ሁለት ቢሊዮን አንድ መቶ ሃምሳ ሦስት ሚሊዮን ስልሳ ሺህ ስድስት መቶ ሰባ አንድ ብር ወጪ የተደረገበት የዓሊ ከተማ-ዋቤ ድልድይና ኮንክሪት አስፋልት መንገድ መጠናቀቁ ተገልጿል።

መንገዱ 56.5 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ሲሆን የአራት ድልድዮች ግንባታና ከባድ የቆረጣ ሥራን በማለፍ በታለመት ጊዜ መጠናቀቁ ተነግሯል። ግንባታው በአጠቃላይ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ማውጣቱ ተገልጿል።

የፕሮጀክቱ ዕውን መሆን ምርቶችን በስፋት እና በጥራት ወደ ማዕከላዊ ገበያ በማድረስ ኢኮኖሚያዊ ፍይዳው የጎላ ሲሆን በዋናነት ሮቤ፣ ዓሊ እና ዋቤ ከተሞችን በቅርበት በማገናኘት፥ የቱሪዝም መዳረሻ የሆኑትን የሶፍ ዑመር ዋሻ፣ የሳነቴ አምባ እና የዲንሾ ብሔራዊ ፓርክ ለጎብኝዎች ምቹ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተገልጿል።

መረጃው የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ነው።

@tikvahethmagazine