Get Mystery Box with random crypto!

በሳኡዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ ዜጎችን ዳግም የማስመለስ ስራ ከ2 ሳምንት በኋላ ይጀመራል | TIKVAH-MAGAZINE

በሳኡዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ ዜጎችን ዳግም የማስመለስ ስራ ከ2 ሳምንት በኋላ ይጀመራል።

ከዚህ ቀደም ከሳዑዲ አረቢያ 102 ሺህ ዜጎችን ለማስመለስ ዕቅድ ተይዞ በ198 በረራዎች  71 ሺህ 697 ሰዎች ማስመለስ የተቻለ ሲሆን ከ2 ሳምንት በኋላ ሥራው ይጀምራል ተብሏል።

በዚህም ሳይመለሱ የቀሩ 30 ሺህ 303 ዜጎችን ከህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለማስመለስ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንና ከመጡ በኋላም የሚያርፉበት ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ  ዝግጁ መደጉ ተገልጿል፡፡

ከዚህ ቀደም ዜጎችን በማስመለስ ሂደት የሌላ አገር ዜጎች እና ሌሎች ግለሰቦች ከተመላሾቹ ጋር በተጭበረበረ ሰነድ ለመግባት ሞክረው  አስቀድሞ በተደረገ የማጣራት ስራ ሊያዙ ችለዋል ነው የተባለው።

ከ16 ሴክተር መስርያ ቤቶች የተውጣጣው ብሄራዊ ኮሚቴው ዜጎችን ለማስመለስ የተሰሩ አጠቃላይ ዝግጅቶችን ዛሬ መገምገሙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አሳውቋል።

@tikvahethmagazine