Get Mystery Box with random crypto!

#Update በኢትዮ- ኬንያ የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር የኮንቨርተር ስቴሽንና የማስተላለ | TIKVAH-MAGAZINE

#Update

በኢትዮ- ኬንያ የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር የኮንቨርተር ስቴሽንና የማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ላይ ኃይል የማስተላለፍ የሙከራ ሥራ በዛሬው ዕለት በስኬት ጀምሯል።

በፕሮጀክቱ ላይ የተተከሉ የተለያዩ የኤሌክትሮ ሜካኒካል መሳሪያዎችንና ዕቃዎችን እንዲሁም የኮሙዩኒኬሽን ዳታ ሲግናሉን በተለያየ ጊዜ የመፈተሸ እና የመሞከር ሥራ ሲሰራ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ኃይል በማስተላለፍ (energize) ከኬንያ ጋር ያለውን ግንኙነት ያለምንም ችግር መሞከር ተችሏል ነው የተባለው።

ከቀናት በፊት የኮሙዩኒኬሽን ሲግናል በመላክ ሲግናሉን ከኬኒያ ኔትወርክ ጋር ማገናኘት የተቻለ ሲሆን የሙከራ ሥራ እየተከናወነ ባለበት ወቅት የግንዛቤ ማስጨበጥ በመሰጠቱ ምንም አደጋ አለማድረሱም ተረጋግጧል።

የግንባታ ሥራው በ2008 የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት እስከ 2000 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፍ አቅም ሲኖረው ግንባታው "CET" በተሰኘ የቻይና ኩባንያ እና ሲመንስ በተሰኘ ኩባንያ በጋራ ተከናውኗል፡፡

በኢትዮጵያ በኩል በተገነባው የኢትዮ - ኬኒያ ባለ 500 ኪሎ ቮልት ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ላይ 994 የመስመር ተሸካሚ ታወሮች የተተከሉ ሲሆን 440 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የኃይል ማስተላለፊያ መስመርና የዳታ ሲግናል ማስተላለፊያ ኬብሎችም ተዘርግተውለታል።

መረጃው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ነው።

@tikvahethmagazine