Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ የተከሰተው ሙሉ የጨረቃ ግርዶሽ (የደም ጨረቃ) ሙሉ የጨረቃ ግርዶሽ ወይም የደም ጨረቃ የሚ | TIKVAH-MAGAZINE

ዛሬ የተከሰተው ሙሉ የጨረቃ ግርዶሽ (የደም ጨረቃ)

ሙሉ የጨረቃ ግርዶሽ ወይም የደም ጨረቃ የሚባለው ጨረቃ ወደ ምድራችን ጥላ ማለትም በፔናምብራው እና አምብራ በተሰኙት የጥላው ክፍሎች ሲያልፉ ከፀሐይ የሚመጣው ብርሃን ነጸብራቅ ነው።

ይህም ከጸሐይ የሚወጣው ነጸብራቅ ሙሉ በሙሉ በምድር በመሸፈን እና በምድር ጫፍ የሚያመልጠው ብርሃን በከባቢ አየሩ ተንጸባቆ ስለሚያልፍ እንደ ሰማያዊ እና ቫዮሌት የመሳሰሉትን ቀለማት በታትኖ ሲያስቀራቸው ቀይና ብርቱካናማ ረጅም የሞገድ  ርዝመት ስላላቸው ከባቢ አየሩን በማለፍ ጨረቃን ይህን ቀለም ይሰጧታል።

በዛሬው ዕለት ለሁለተኛ ጊዜ የተከሰተው ይህ ሙሉ የጨረቃ ግርዶሽ ለ85 ደቂቃዎች የቆየ ሲሆን በ ሰሜን አሜሪካ፣ በአንዳንድ የደቡብ አሜሪካ ክፍሎች፣ በኤስያ፣ በአውስትራሊያ እና በኒውዝ ላንድ ታይቷል።

* መረጃውን የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ የላከልን ሲሆን ፎቶው በቤጂንግ የተከሰተና ከAFP የተገኘ ነው።

@tikvahethmagazine