Get Mystery Box with random crypto!

'በህጋዊ 5 መቶ ብር ሃሰተኛ 1ሺ 500 ብር እንደሚቀይሩ በምርመራ ተረጋግጧል' ፡ ፖሊስ በሀሰተ | TIKVAH-MAGAZINE

"በህጋዊ 5 መቶ ብር ሃሰተኛ 1ሺ 500 ብር እንደሚቀይሩ በምርመራ ተረጋግጧል" ፡ ፖሊስ

በሀሰተኛ ገንዘብ ሲገለገሉ ተይዘው ምርመራ በተደረገባቸው 4 ተማሪዎች መነሻነት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ካዛንቺስ አፍሪካ ዳቦ ቤት እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው የተጠርጣሪ ቤት በህግ አግባብ በተደረገ ፍተሻ 13ሺ 200 ሃሰተኛ ብር እና ብሩን ለማዘጋጀት የሚጠቀምባቸውን የተለያዩ ቁሳቁሶች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ተማሪዎቹ ሃሰተኛ ባለ 2 መቶ የብር ኖት ይዘው በሚማሩበት ትምህርት ቤት መዝናኛ ክበብ ግብይት ለመፈፀም ሲሞክሩ የክበቡ ባለቤት ተጠራጥረው ጉዳዩን ለፖሊስ በማሳወቃቸው ተማሪዎቹን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ የማጣራት ስራ መሰራቱ ነው አስታውቀዋል።

በተማሪዎቹ ላይ በተደረገው ምርመራ ሃሰተኛ ገንዘቡን ከሚዘጋጀው ግለሰብ በህጋዊ 5 መቶ ብር ሃሰተኛ 1ሺ 500 ብር እንደሚቀይሩ በምርመራ መረጋገጡን የላንቻ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ስለሺ ሸንቁጤ ገልጸዋል።

ከአራቱ ተማሪዎች በተጨማሪ ሃሰተኛ ገንዘቡን ሲያዘጋጅ የነበረው ግለሰብ እና በግብራበርነት የተሳተፉ 2 ተጠርጣሪዎች በአጠቃላይ 7 ግለሰቦች ተይዘው የምርመራው ሂደት መቀጠሉን ፖሊስ ገልጿል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot