Get Mystery Box with random crypto!

ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የኦንላይን (Online) ሙከራ ፈተና የሰጠው ት/ቤት በሀገር ደረጃ ለመጀ | TIKVAH-MAGAZINE

ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የኦንላይን (Online) ሙከራ ፈተና የሰጠው ት/ቤት

በሀገር ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የኦንላይን (Online) ሙከራ ፈተና መስጠቱን የአረካ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስታዉቋል። ይህም ሀገራዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች በፈተና ጊዜ የቴክኖሎጂ ችግር እንዳይገጥማቸው ያግዛል ነው የተባለው።

ፈተናው በሙክራ እየተሰጠ የሚገኘው ትምህርት ቤቱ በራሱ መምህር አማካኝነት በበለጸገው ሥርዓት አማካኝነት ነው። ትምህርት ቤቱ የዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ በተገኙበት በይፋ በዛሬው ዕለት ሲስተሙን አስተዋዉቋል።

የወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ታደሰ ኩማ ይህ ተግባር እጅግ ተስፋ የሚሰጥ ተግባር መሆኑን በመግለፅ የዚህን ትምህርት ቤት ተሞክሮ ወደ ሌሎች በዞን ወደሚገኙ ትምህርት ቤቶች በአጭር ጊዜ ለማስፋፋት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

ይህ የኦንላይን (Online) ፈተና ዝግጅት ከማዳበር ባሻገር ለተማሪዎች የቴክኖሎጂ ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩና እንድያጎለብቱ መልካም እድል እንደሆነ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ አለማየሁ ተናግረዋል።

ትምህርት ቤቱ በዚህ ዘርፍ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የጠቀሱት አቶ አለማየሁ በረካታ በጀቶችን ወደዚህ መስክ በማሰማራት ዉጤታማ ለመሆን እየተሰራ እንደሚገኝ ጭምር ጠቁመዋል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot