Get Mystery Box with random crypto!

በመዲናዋ የቱሪስት ፖሊስ ለማቋቋም የሚያስችል መነሻ ሰነድ ላይ ውይይት ተካሄደ። የአዲስ አበባ ባ | TIKVAH-MAGAZINE

በመዲናዋ የቱሪስት ፖሊስ ለማቋቋም የሚያስችል መነሻ ሰነድ ላይ ውይይት ተካሄደ።

የአዲስ አበባ ባህል፣ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ በከተማ ደረጃ የቱሪስት ፖሊስ ለማቋቋም የሚያስችል መነሻ ሰነድ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማካሄዱን ገልጿል።

መነሻ ሰነዱን ያቀረቡት የቢሮው የቱሪዝም መዳረሻ ልማት ቡድን መሪ አቶ ሳምሶን አይናቸው ከተማዋ ካላት እምቅ የቱሪስት መስህብ ሀብት ለመጠቀም የቱሪስትን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የቱሪስት ፖሊስ በተቋም ደረጃ ማደራጀት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሳው በቱሪዝም ዘርፉ ያለውን ብዛት የለው መስህብ ለቱሪስቱ ተደራሽ ለማደረግ ደህንነቱ የተጠበቀና አስተማማኝ ሰላም ያለባት ለማደረግ የቱሪስት ፖሊስ እንደሚያስፈልግ በመገንዘብ ወደ ስራ እንደተገባ ገልፀው ቱሪስት ፖሊስ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ እንሰራለን ብለዋል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot