Get Mystery Box with random crypto!

#የዛሬ (ሰኔ 2/2014) በኮትዲቫር አዘጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በምድብ አ | TIKVAH-MAGAZINE

#የዛሬ (ሰኔ 2/2014)

በኮትዲቫር አዘጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በምድብ አራት ላይ በቢንጉ ብሄራዊ ስታዲየም በተካሄደ ጨዋታ #የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከ ግብፅ ጋር ያደረገውን ጨዋታ ከጨዋታ ብልጫ ጋር 2 - 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የዋልያዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ዳዋ ሁቴሳ እና አምበሉ ሽመልስ በቀለ አስቆጥረዋል። ዋልያዎቹ ከ እ.ኤ.አ 1989 በኋላ በኋላ የግብፅ ብሄራዊ ቡድንን ማሸነፍ ችሏል።

የዛሬው ውጤት ተከትሎ ሀገራችን በሶስት ነጥብ አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ሀገራችን #ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር ያደረገችውን ፍልሚያ በማሸነፏ፤ ማላዊ ደግሞ በጊኒ በመሸነፏ ምድቧን #በአንደኛነት መምራት ጀምራለች።

በሀገራችን የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና የአዛን ውድድር የፊታችን እሁድ ይካሄዳል። ሰኔ 5/2014 በአዲስ አበባ ስቲዲዮም ለሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና የአዛን ውድድርም በርካታ እንግዶች እየገቡ ይገኛሉ። ሀገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያስጠራው ይህ ውድድር ከ56 በላይ ሀገራት የሚወዳደሩበት ሲሆን ለውድድሩ ከፍተኛ ዝግጅት ሲካሄድ ቆይቷል ተብሏል።

ዛሬ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከልዑካቸው ጋር ለአዲሱ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት በዓለ ሲመት ለመታደም ሞቃዲሾ ተገኝተዋል። በበዓለ ሲመቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) #ኢትዮጵያ ለአዲሱ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ያላትን ድጋፍ አረጋግጠዋል። በሶማሊያ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በማየታቸውም ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የፓስፖርት አገልግሎት ክፍያዎችን በ " ቴሌ ብር " አማካኝነት መፈፀም እንዲቻል በኢትዮ ቴሌኮም እና በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መካከል ዛሬ ስምምነት ተፈፅሟል።

ድንበር የለሽ ዶክተሮች (MSF) በአፋር ክልል እየጨመረ የመጣው የምግብ እጥረት ቀውስ ስጋት እንዳጫረበት ገልጿል። ድርጅቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች መሠረታዊ የሚባሉ የጤና ማዕከላትን እንዲሁም ንጹህ የመጠጥ ውሃ በማያገኙበት ሁኔታ ነው የሚኖሩት ብሏል። በተጨማሪም በርካታ ሕፃናት በከፋ የምግብ እጥረት ሕይወታቸውን አጥተዋል ሲል አመልክቷል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ሰለሞን ሹምዬ እና መዓዛ መሐመድ በስር ፍርድ ቤት የተፈቀደላቸውን የ10 ሺህ ብር ዋስትና ሽሯል። ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን የሻረው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በዋስትና ትዕዛዙ ላይ ይግባኝ ካቀረበ በኋላ ነው። የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 2 ቀን 2014 ከሰዓት በጽህፈት ቤት በኩል በሰጠው ትዕዛዝ ለመርማሪ ፖሊስ የ8 ቀናት የምርመራ ጊዜን ፈቅዷል።

የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዛሬ ሰኔ 2 ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት የብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ ተመልክቷል። በዚህም፥ የጊዜ ቀጠሮውን ጉዳይ መርማሪ ፖሊስ ምርመራየን ጨርሸ የምርመራ መዝገቡን ለዐቃቢ ህግ ለመላክ በዝግጅት ላይ ነኝ ያለ ሲሆን የክልል ዐቃቤ ህግ በችሎት ቀርቦ አዎ ምርመራው አልቋል የክስ መመስረቻ ጊዜ 15 ቀናት ይሰጠኝ ሲል ጠይቋል። የዋስትና ጥያቄውም ላይ ብይን ለመስጠት ለነገ ለሰኔ 3/2014 ዓ/ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot