Get Mystery Box with random crypto!

በድሬዳዋ የጎርፍ አደጋ ስጋት በመኖሩ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች ላይ የቅድመ ጥንቃቄ ሥራ አየተሰራ | TIKVAH-MAGAZINE

በድሬዳዋ የጎርፍ አደጋ ስጋት በመኖሩ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች ላይ የቅድመ ጥንቃቄ ሥራ አየተሰራ ነው ተባለ።

ከሐምሌ ወር አጋማሽ እስከ ነሀሴ መጨረሻ ድረስ ባሉት ሳምንታት ከፍተኛ ዝናብ እንደሚጥል ከሜትሮሎጂ ኤጀንሲ የተገኘው መረጃ ያሳያል። በዚህም በድሬዳዋ ከተማ የጎርፍ አደጋ እንደሚያሰጋት ተገልጿል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሀለኒ ሀሰን በከተማው ያሉ ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን በመለየት በተለይ በሶስት ወንዞች አካባቢ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።

በወንዞ ዳርቻ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች አስቀድመው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና በተለይም የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ቤቶችን በመለየት ጥናት እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ድሬዳዋ በተደጋጋሚ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ እንደመሆኗ በተለዩ አካበቢዎች መጠነ ሰፊ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ኮሚሽነር አቶ ሀለኒ ሀሰን ተናግረዋል፡፡

ተዳፋት የመሬት አቀማመጥና ተፋሰስ አካባቢዎች በክረምቱ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በመሆናቸው ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የሚያስችል በከተማዋ ግብረሀይል ተቋቁሞ እየተሰራ ይገኛል፡፡በድሬዳዋ ከተማ ከ16 ዓመታት በፊት በ1998 ዓ.ም ባጋጠመ ከባድ የጎርፍ አደጋ ከ250 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል፡፡

Credit : Bisrat FM 101.1

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot