Get Mystery Box with random crypto!

#Jimma የጅማ ዩኒቨርሲቲ የአደጋ ግዜ አስቸኳይ ምላሽ ቡድን እና የጅማ ከተማ ጤና ጥበቃ ጽ | TIKVAH-MAGAZINE

#Jimma

የጅማ ዩኒቨርሲቲ የአደጋ ግዜ አስቸኳይ ምላሽ ቡድን እና የጅማ ከተማ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት በመተባበር ያዘጋጁት በድንገተኛ አደጋ ግዜ ቁጥጥርና ምላሽ አሰጣጥ ዙርያ የሚካሄደው የመስክ ሙከራ ነገ ስለሚካሄድ ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ የአንቡላንሶች እንቅስቃሴና ድምፅ(ሳይረን)፣ እንድሁም የጤና የባለሙያዎች እንቅስቃሴ እንደሚኖር ተገልጿል።

በዚህም፥ በከተማዋ ከጧቱ 3 ስዓት እስከ ከቀኑ 6 ሰዓት በሚኖረው እንቅስቃሴ ህብረተሰቡ እንዳይደናገጥ የጅማ ከተማ ከተማ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት መልዕክት አስተላልፏል።

የእንቅስቃሴዎቹ ስፍራዎች፦

1.ከጅማ ዩኒቨርስቲ ትልቁ ስታዲየም
2.የጅማ ዩኒቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል
3. ሸኔን ግቤ ሆስፒታል
4.የጅማ ጤና ጣቢያ

ሁሉም አካላት እንቅስቃሴዉ በሚደረግባቸዉ በሁሉም ስፍራዎች ለአንቡላንሶችና ለጤና ባለሞያዎች የቀና ትብብር እንድያድርጉም ተጠይቋል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot