Get Mystery Box with random crypto!

#የዛሬ (23/2014) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል፤ በጋምቤላ ክልል በአኙዋ ብሔ | TIKVAH-MAGAZINE

#የዛሬ (23/2014)

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል፤ በጋምቤላ ክልል በአኙዋ ብሔረሰብ ዞን በዲማ ወረዳ፤ በአማራ ክልል በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጓንጓ ወረዳ 8 ቀበሌዎች በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ በሁሉም ቀበሌያት በሰብሎች ላይ #ተምች መከሰቱ ተገልጿል። በአብዛኞቹ አከባቢዎች ተምቹ በሰብሉ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ተሰግቷል።

የኢትዮጵያ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ህወሃት " የኤርትራ ጦር ጥቃት ከፈተ " በሚል የሚያሰራጨው መረጃ ትክክል አይደለም ብለዋል። በኤርትራና በህወሃት መካከል ግጭት እንዲፈጠር ያደረገው እራሱ ህወሃት ነው ሲሉም ተናግረዋል። ትላንት ህወሓት ባሰራጨው መረጃ ባለፈው ቅዳሜ እና እሑድ የኤርትራ ሠራዊት በሽራሮ ጥቃት ከፍቶ እንደነበር እንዲሁም ከ4 ቀን በፊት በአዲአዋላ ውጊያ መደረጉን አሳውቆ ነበር።

ሮይተርስ ዛሬ ይዞት በወጣው ዘገባ ባለፈው ሳምንት የመጨረሻ ቀናት ላይ የኤርትራ ጦር በሽራሮ ከተማ ላይ በከፈተው ጥቃት አንዲት የ14 ዓመት ታዳጊ መገደሏን እና 18 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን አመልክቷል።

የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት መቋጫ ያገኝ እና አስተማማኝ ሰላም ይሰፍን ዘንድ ጥረት እያደረጉ የሚገኙ የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞ ናይጄሪያ ፕሬዜዳን ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ትግራይ ክልል ይገኛሉ። ኦባሳንጆ እና ዶ/ር ደብረፅዮን በቀጠናዊ ጉዳዮች ጋር መምከራቸው የተነገረ ሲሆን ምክክሩን የተመለከተ ዝርዝር መረጃ ይፋ አልሆነም።

በናይጄሪያ አንድ የ40 ዓመት ጎልማሳ በዝንጀሮ ፈንጣጣ / Monkeypox መሞቱን የሀገሪቱ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል (NCDC) ትላንት ምሽት አስታውቋል። በናይጄሪያ ከሚገኙት 36 ግዛቶች ዘጠኙ የዝንጀሮ ፈንጣጣ (MonkeyPox) ተመዝግቦባቸዋል። በሌላ በኩል በኮንጎ በ2022 9 ሰዎች በበሽታው መሞታቸው ሪፖርት መደረጉን ዋሽንግተን ፖስት አስነብቧል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የቀጠለ ሲሆን ፤ በግንቦት 23/2014 ዓ/ም ውሎ የደቡብ ክልል ፕሬዝደንት እና ሌሎች የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች በምልዓተ ጉባኤው ተገኝተው በቤተክርስቲያን ላይ በየጊዜው እየደረሱ ባሉ ችግሮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል። በክልሉ ያሉ ችግሮች በደብዳቤ ንባብ እንዲሁም በክልሉ በሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት አማካይነት የቃል ጥያቄ ቀርቦ ምላሽ እንዲያገኙም ተጠይቋል። የክልሉ ፕሬዝደንት የተፈጠሩትን ችግሮች ለመፍታት አስተዳደሩ እያደረጋቸው ያሉ ጥረቶችን አስረድተው፥ በየደረጃው ለመፍታት እንደሚሠሩ ገልፀዋል።

ዛሬ በኦሮሚያ ክልል በሰበታ ከተማ 100 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የፈጀ የኮካኮላ ምርት ማምረቻ ፋብሪካ ተመርቋል። ፋብሪካው በዓመት 100 ሚሊየን በላይ እሽግ ለስላሳ ለማምረት ያስችለዋል የተባለ ሲሆን የማምረቻ ግብዓቶችን በማምረትም ከውጪ ወደ ሀገሪቷ የሚገቡ ምርቶችን ይቀንሳልም ተብሏል። ኮካ ኮላ " ሚኒት ሜድ " የተሰኙ የጁስ ምርቶቹን ወደ ኢትዮጵያ ገበያ እያመጣ መሆኑን ዛሬ በነበረው የፋብሪካው ምረቃ ሥነ-ስርአት ላይ ተሰምቷል።

በደሴ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ ትላንት ከምሽቱ 5:30 አካባቢ በተለምዶ ሙጋድ አካባቢ በተነሳው መንስዔው ያልታወቀ የእሳት ቃጠሎ 6 ሰዎች ከመጎዳታቸው በተጨማሪ 24 መኖሪያ፣7 የንግድና ድርጅት ቤቶች ከእነ ሙሉ ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ፖሊስ አረግጧል። በቃጠሎው በከባድ መሳሪያ ተተኳሽ ቅሪቶች ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ የነበረው ፍንዳታ ህዝብ እንዳይጠጋ መሠናክል ሆኖበት አምሽቷል ተብሏል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot