Get Mystery Box with random crypto!

ለጉልበት ብዝበዛ 13 ህጻናትን አሳልፎ ለመሸጥ ሲሞክሩ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ። | TIKVAH-MAGAZINE

ለጉልበት ብዝበዛ 13 ህጻናትን አሳልፎ ለመሸጥ ሲሞክሩ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ።

በባሌ ዞን 13 ህጻናትን ከምዕራብ አርሲ ሻሸመኔ ወረዳ በማምጣት ዞኑ ሲናና ወረዳ ላይ ለጉልበት ብዝበዛ (በከብት ጥበቃ፣ለቤት ሰራተኝነት እና ለንግድ ቤት) እያንዳንዳቸዉን በሶስት ሺህ ብር ለመሸጥ ሲሞክሩ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በእስራት ተቀጥተዋል ተብሏል።

አንደኛ ተከሳሽ ጀማል ሱሳ እንዲሁም ሁለተኛ ተከሳሽ ሂርጶ ዲማ በምዕራብ አርሲ ዞን ሻሸመኔ ወረዳ አባሮ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ አስር ወንድ እና ሶስት ሴት ህጻናትን በህገወጥ መንገድ ወደ ባሌ ሲያጎጉዙ በአንድ ህጻን ላይ በተፈጠረ የዋጋ አለመግባባት ምክኒያት ህብረተሰቡ ለፖሊስ ባደረሰው ጥቆማ ተጠርጣሪዎቹ ሊያዙ መቻላቸዉ ተገልጿል፡፡

ፖሊስ ጉዳዩን ሲከታተል ቆይቶ መዝገቡን ለባሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረበው መሰረት ፍርድ ቤቱ በመጀመሪያ ተከሳሽ ጀማል ሱሳ ላይ በአስራ ስምንት ዓመት እስራት እንዲሁም በሁለተኛ ተከሳሽ ሂርጶ ዲማ ላይ ደግሞ የአስር ዓመት እስራት ወስኖባቸዋል፡፡

የባሌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኮሚኒኬሽን ባለሙያ የሆኑት ኮማንደር ናስር ዑመር ለብስራት ኤፍ ኤም እንደገለጹት በደቡብ ክልል እና በምዕራብ አርሲ ዞን ህገወጥ የህጻናት ዝውውር በከፍተኛ መጠን እየጨመረ በመሆኑ የሚመለከተው አካል ለጉዳዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል።

Credit : Bisrat Fm 101.1

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot