Get Mystery Box with random crypto!

#Benishangulgumuz በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን በማንዱራ፣ ዳንጉር እና | TIKVAH-MAGAZINE

#Benishangulgumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን በማንዱራ፣ ዳንጉር እና ፓዊ ወረዳዎች የ76 ንጹሃን ዜጎችን ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲጠፋ ያደረጉ ተከሳሾች እንደየወንጀል ተሳትፏቸው ከእድሜ ልክ ጀምሮ በጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ፡፡

ተከሳሾቹ በተጠቀሱት አካባቢዎች የእርስ እርስ ጦርነት እንዲነሳና ብሔር-ተኮር ግጭት እንዲቀሰቀስ በማድረግ የ76 ንጹሃን ዜጎች ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲጠፋና ከፍተኛ ንብረት እንዲወድም ማድረጋቸው ተነግሯል።

ተከሳሾች ዜጎችን ወይም በአገር ነዋሪ የሆኑትን በማሰታጠቅ፣ በወረዳዎቹ በ2011 ዓ.ም ከታህሳስ እሰከ ሰኔ ወር አጋማሽ ድረስ ብሔር ተኮር ግጭትን ቀስቅሰዋል፡፡

በ20 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት እንዲደርስ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቤት ንብረታቸዉ እንዲፈናቀሉ በማድረግ እና ግምቱ ከፍተኛ የሆነ ንብረት እንዲዘረፍ እና እንዲወድም በማድረግ የወንጀል ድርጊት ዉስጥ በመሳተፋቸው በፈጸሙት ወንጀል በዓቃቤ ህግ ተከሰዋል፡፡

የፌዴራል ዓቃቤ ህግ የተከሳሾችን ጥፋተኝነት የሚያረጋግጡ ማስረጃዎቹን አቅረቦ ለፍርድ ቤቱ ያሰማ ሲሆን÷ ጉዳያቸውን ሲከታተሉ ከነበሩ 29 ተከሳሾች መካከል 3ቱ የቀረበባቸውን ክስ እና ወንጀል መከላከል በመቻላቸው በነጻ ተሰናብተዋል፡፡

ግንቦት 12 ቀን 2014 ዓ.ም. በዋለዉ ችሎት 4 ተከሳሾች ላይ የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት፤ 1 ተከሳሽ በ 25 ዓመት፤ 1 ተከሳሽ በ 23 ዓመት ጽኑ እስራት፤ 17 ተከሳሾች በ 22 ዓመት፤ 2 ተከሳሾች በ 20 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡና 1 ተከሳሽ ዕድሜዉ ለአካለ መጠን ያልደረሰ በመሆኑ በልዩ ሁኔታ በ 8 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ፈርዷል። እንዲሁም ሁሉም ተከሳሾች ከሲቪል መብቶቻቸዉ ለ 5 ዓመት መታገዳቸውን ፍትሕ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

@tikvahethmagazine