Get Mystery Box with random crypto!

#የዛሬ (ግንቦት 12/2014) በሲዳማ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ዳግም የፀ | TIKVAH-MAGAZINE

#የዛሬ (ግንቦት 12/2014)

በሲዳማ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ዳግም የፀጥታ ችግር እና ግጭት አገርሽቶ የሰዎች ህይወት ማለፉን የአከባቢው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ከበንሳ ጠቁመዋል። ከሁለቱም ክልል የሚመለከተው አካል እንዲሁም የፌደራል መንግስት የህዝቡን ደህንነት እንዲያስጠብቅና ግጭቱን እንዲቆም መፍትሄ እንዲፈለግም አሳስበዋል።

በ2021 በኢትዮጵያ ግጭት እና ሁከት ከ5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል። ይህ ቁጥር ከቀደመው ዓመት በ3 እጥፍ ይበልጣል። በIDMC ሪፖርት መሠረት በትግራይ ክልል 1.8 ሚሊዮን፣ በአማራ ክልል 1.7 ሚሊዮን፣ በኦሮሚያ ክልል 643 ሺ ተፈናቃዮች ተመዝግበዋል። ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሀራ በርሀ በታች በሚገኙ አገራት የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ14 ሚሊዮን በላይ ደርሷል።

የብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ " ህገ መንገስቱን በኃይል በመናድ ወንጀል " በሚል ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ሂደቱን የተመለከተው የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት የፌደራል ፖሊስ ከጠየቀው የ14 ቀን ውስጥ 10 ቀን በመፍቀድ ለግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በህንድ አዘጋጅነት ለሚካሄደው የአለም ከ 17 አመት በታች የሴቶች የአለም ዋንጫ ለማለፍ በአፍሪካ ዞን እየተደረገ በሚገኘው የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ የሴቶች ከ 17 አመት ብሄራዊ ቡድን በናይጄሪያ አቻው 1 : 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል። ቡድኑ ግንቦት 27 በናይጄሪያ በሚካሄደው የመልስ ጨዋታ ላይ ውጤቱን መቀልበሰ ከቻለ በህንድ አዘጋጅነት በሚካሄደው የአለም ዋንጫ ላይ ተሳታፊ መሆናቸውን የሚያረጋግጡ ይሆናል።

ትላንት ሀሙስ አመሻሽ ላይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ስር ከሚገኘው የአሶሳ ማረሚያ ቤት 17 ተጠርጣሪዎች ማምለጣቸውን የዞኑ ማረሚያ ቤት መምሪያ አሳውቋል። ከማረሚያ ቤቱ ያመለጡት ግለሰቦች " በወቅታዊ ሁኔታ እና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት " ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ናቸው ተብሏል። ከዚሁ ማረሚያ ቤት ከሶስት ወር በፊት የቀድሞው የቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ መሪ አቶ አብዱልዋሀብ መሀዲ በተመሳሳይ ሁኔታ ማምለጡ ይታወሳል።

'ሴንሆን የማር ምርቶች' እና 'ሮም የገበታ ጨው ' የጤና ብቃት ማረጋገጫ ባለማግኘታቸው ከገበያ እየተሰበሰቡ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን አሳውቋል።

በኢትዮጵያ ውስጥ በኮሜዲ ዘርፍ ከታዩ እጅግ ተወዳጅ እና ምርጥ ኮሜዲያኖች እንዱ እንደሆነ የሚነገርለት ኮሜዲያን ወንድወሰን ብርሃኑ ( #ዶክሌ ) በ57 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየቱ ተሰምቷል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከማላዊ እና ግብፅ ጋር ለሚያደርጋቸው የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ዝግጅት ለሀያ ስምንት ተጫዋቾች ጥሪ ተደርጓል፡፡ ዋልያዎቹ ግንቦት 25 እና 29 ከማላዊ እና ግብፅ ብሔራዊ ቡድኖች ጋር የ 2023 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ የጨዋታቸውን በቢንጉ ስታዲየም የሚያከናውኑ ይሆናል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ.ም የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት የአካዳሚክ ካላንደር ማሻሻያ ያደረገ ሲሆን የ8ኛ ክፍል ከተማ ዐቀፍ ፈተና ከሰኔ 27 እስከ 29/2014 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል ብሏል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot