Get Mystery Box with random crypto!

#Awaday #Gondar ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እያካሄደ የሚገኘውን የሙከራ ኔትዎርክ አገልግሎቱን እ | TIKVAH ETHIOPIA

#Awaday #Gondar

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እያካሄደ የሚገኘውን የሙከራ ኔትዎርክ አገልግሎቱን እያስፋፋ ይገኛል።

ዛሬ በተላከልን መልዕክት ፤ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በአወዳይ እና ጎንደር ከተሞች አስጀምሯል።

ይህ የደንበኞች ሙከራ የሳፋሪኮምን ኔትወርክ እየሞከሩ ያሉትን ከተሞች ቁጥር 10 አድርሶታል። ከዚህ በፊት በድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሐረማያ፣ ባሕር ዳር፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ሞጆ እና ደብረ ብርሃን ላይ ሙከራ መጀመሩ ይታወቃል።

የአወዳይ እና ጎንደር ደንበኞች የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የአየር ሰዓት እና የስልክ ቀፎዎች ግዢ እንዲሁም የደንበኞች ድጋፍ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።

በአወዳይ አንድ በቀበሌ ዐ1 የሚገኝ የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈበት መደብር እና በጎንደር አራት (በፒያሳ፣ አራዳ፣ አዘዞ እና ኮሌጅ) የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈባቸው መደብሮች ደንበኞችን ለማገልገል ክፍት ናቸው ሲል በላከልን መልዕክት አሳውቋል።

@tikvahethiopianss