Get Mystery Box with random crypto!

#ድርድሩ በአዲስ አበባ ከፌዴራል መንግስት ጋር እንዲሁም መቐለ ተጉዘው ትግራይ ክልልን እያስተዳደ | TIKVAH-ETHIOPIA️🇪🇹-(2)

#ድርድሩ

በአዲስ አበባ ከፌዴራል መንግስት ጋር እንዲሁም መቐለ ተጉዘው ትግራይ ክልልን እያስተዳደረ ካለው ህወሓት ጋር ሰሞኑን የተወያዩት የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አኔቴ ዌበር ከጀርመን ሬድዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በፌዴራል መንግስት እና ህወሓት መካከል ይደረጋል ተብሎ ለሚጠበቀው የሰላም ድርድር " የመተማመን መጥፋት " መሰናክል መሆኑን ተናግረዋል።

ዌበር ለሬድዮ ጣቢያው " ዋነኛው መሰናክል (ለሰላም ድርድሩ) የእምነት እጦት ነው ብዬ አስባለሁ። አንዱ ከሌላው ጋር በቅን ልቦና እየተደራደሩ ለመሆናቸው የበለጠ መተማመኛ እንደሚፈልጉ 2ቱም ግልፅ አድርገዋል።

ሁለቱ ወገኖች ዝግጁነታቸውን ከማሳወቅ ባሻገር ወደ ድርድሩ እንዲመጡ የሚያስፈልገውን መተማመን የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ያጠናክራሉ ብዬ ተስፋ አድርጋለሁ።

የፌዴራል መንግስት ተጨማሪ ቅድመ ሁኔታዎች እንደሌሉት አረጋግጧል። ከመንግስት በኩል የተቋረጡ መሰረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ ለማስጀመር ምልክት ከሰጠ ወይም ካስጀመረ ህወሓት በጠረጴዛ ዙሪያ ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን በመቐለ ጉብኝታችን ተረድቻለሁ " ሲሉ ተናግረዋል።

የተቋረጡ መሰረታዊ አገልግሎቶችን በተመለከተ ዌበር በጥቂት ቀናት ውስጥ ስራ ይጀምራሉ የሚል ተስፋ እንዳላቸው ከሬድዮ ጣቢያው ጋር በነበራቸው ቃለምምልስ ወቅት ተናግረዋል።

ዌበር " እኛ አሁን እጅግ በቅርቡ ተግባራዊ ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

መሰረታዊ አገልግሎቶች ስራ ከሚጀምሩበትን፤ መጀመራቸውን እየተጠባበቅን ነው። በዚህ ረገድ ከአዲስ አበባም ሆነ ከመቐለ የተቀየረ ነገር ካለ አልሰማሁም፤ ነገር ግን ይህ በማንኛውም ቀን ተግባራዊ ይሆናል ብዬ እጅግ ተስፋ አደርጋለሁ። " ብለዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/EU-08-05