Get Mystery Box with random crypto!

#HappeningNow ኢትዮ ቴሌኮም ቴሌብር መላ፤ ቴሌብር እንደኪሴ እንዲሁም ቴሌብር ቁጠባ የተሰ | TIKVAH-ETHIOPIA️🇪🇹-(2)

#HappeningNow

ኢትዮ ቴሌኮም ቴሌብር መላ፤ ቴሌብር እንደኪሴ እንዲሁም ቴሌብር ቁጠባ የተሰኙ የፋይናንሻል አገልግሎቶችን ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል።

ቴሌ ብር መላ፦ የቴሌብር ደንበኞቹን ባንቀሳቀሱት የገንዘብ ዝውውር መሰረት ታይቶ እስከ በቀን እስከ 2,000 በወር ደግሞ እስከ 10,000 ብር የሚደርስ ብድር የሚያመቻች አገልግሎት ነው።

ቴሌ ብር እንደኪሴ ፦ በቴሌብር አማካኝነት ግብይት በሚፈጸምበት ጊዜ የቴሌብር ሂሳቦ ከሚገዙት እቃ በታች ከሆነ ቀሪውን ክፍያ ጨምሮ ለሻጭ ይከፍልና ገንዘብ ገቢ ሲያደርጉ ከሂሳቦ ላይ ተቀናሽ የሚያደርግ አገልግሎት ነው።

ቴሌብር ቁጠባ፦ ቴሌብር ላይ ካለው የገንዘብ መጠን ላይ መቆጠብ የሚያስችል አገልግሎት ሲሆን በሁለት አማራጮች ማለትም በወለድና ያለወለድ የቀረበ ነው። የወለድ መጠኑም 7% ሲሆን ወለዱ መጠን በቀን ተሰልቶ በሂሳቦ ገቢ ይደረጋል።

ተጨማሪ መረጃ እንልክላችኃለን!