Get Mystery Box with random crypto!

' ... አልሸባብ ዳግመኛ ወደ ድንበር እንዳይጠጋ የማረጋገጥ ስራ እየተሰራ ነው ' - የሶማሌ ክል | TIKVAH-ETHIOPIA️🇪🇹-(2)

" ... አልሸባብ ዳግመኛ ወደ ድንበር እንዳይጠጋ የማረጋገጥ ስራ እየተሰራ ነው " - የሶማሌ ክልል ፕ/ት ሙስጠፌ ሙሁመድ

በቅርቡ በኢትዮጵያና ሶማሊያ ድንበር ላይ ጥቃት ፈፅሞ የነበረው የአልሸባብ ቡድን 800 ታጣቂዎቹ መገደላቸውን 100 የሚጠጉት ደግሞ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሶማሌ ክልል ፕሬዜዳንት ሙስጠፌ ሙሁመድ በተረጋገጠ ትዊተር ገፃቸው ላይ አሳውቀዋል።

የአልሸባብ ጥቃት በሽንፈት መጠናቀቁን የገለፁት ፕሬዜዳንት ሙስጠፌ አልሸባብ ዳግመኛ ወደ ድንበር እንዳይጠጋ እና እንዳይዳፈር የማረጋገጥ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
@tikivah_ethiopiaa