Get Mystery Box with random crypto!

' ፍትህ ይሰጠኝ ፣ ህግ ይፍረደኝ ' - ወላጅ አባት ከሰሞኑን በአ/አ በአንድ የግል ከፍተኛ ትም | TIKVAH-ETHIOPIA️🇪🇹-(2)

" ፍትህ ይሰጠኝ ፣ ህግ ይፍረደኝ " - ወላጅ አባት

ከሰሞኑን በአ/አ በአንድ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ውስጥ አንድ ተማሪ እጅግ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ተገድሏል። ጉዳዩ ምንም እንኳን በህግ ቢያዝም ቤተሰቦች ተገቢውን ፍትህ እንዲያገኙ ጠይቀዋል።

በሚማርበት ተቋም ውስጥ የተገደለው ተማሪ ዮሐንስ አሰፋ ይባላል።

ተማሪ ዮሐንስ እድሜው 20 እስከ 12ኛ ክፍልም በኮከበፅብአ ት/ቤት ትምህርቱን ተከታትሏል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ውጤት አምጥቶም ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ቢመደብም አባት አቅም ስለሌላቸውና አጠገባቸው እንዲሆን ቅ/ማርያም ዩኒቨርሲቲ (ዋቢ ሸበሌ) ትምህርቱን እንዲጀምር ያደርጋሉ።

ዮሐንስን ትምህርቱን (በአካውንቲንግ) በከፍተኛ ውጤት እየተከታተለ 2 ዓመት ድረስ መድረስ ችሏል።

የተማሪውን ባህሪ የሚያውቁ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላትና የዮሐንስ ወላጅ አባት ልጃቸው ከሰው ጋር የማይጋጭ፣ በቤተክርስቲያን አስተምሮ ያደገ፣ የቤተክርስቲያን አገልጋይ፣ ጨዋና ሰዎችን ቀና ብሎ የማያይ እንደሆነ ገልፀዋል።

ነገር ግን ከሰሞኑን በትምህርት ተቋሙ ውስጥ በርካታ የሰውነቱ ቦታ ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት ተወጋግቶ ተገድሏል።

አባት፤ "ልጄ እንደበግ ነው የታረደው" ያሉ ሲሆን "ህግ ፍትህ ይስጠኝ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረደኝ ፣ የልጄ ደም ይውጣልኝ፤ ህግ ካለ መንግስት ካለ ፍትህ ይስጠኝ" ብለዋል።

ወላጅ አባት ጉዳዩ በህግ እንደተያዘ ገልፀው " ህግ ይፍረደኝ የልጄን ደም ይፈልግልኝ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረደኝ፤ ንፁህ ኢትዮጵያዊ በኤርትራ ምድር ደሜ ፈሷል ቆስያለሁ ቆስዬ ጡረታም የለኝ፣ የምሰራው በአትክልተኝነት ነው ልጄን በብዙ ችግር ነው ያሳደኩት የኢትዮጵያ ህዝብ ይሄን አይቶ ይፍረደኝ" ሲሉ ተማፅነዋል።

ያንብቡ telegra.ph/Yohannes-Asefa-08-06