Get Mystery Box with random crypto!

የውጭ ባንኮች እንዲገቡ የሚፈቅደው ረቂቅ አዋጅ ማሻሻያ ተጠናቀቀ። የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ለው | Think Abyssinia

የውጭ ባንኮች እንዲገቡ የሚፈቅደው ረቂቅ አዋጅ ማሻሻያ ተጠናቀቀ

የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ለውጭ ተወዳዳሪዎች ክፍት እንዲሆን ከተወሰነ በኋላ፣ በ2009 ዓ.ም. የወጣው የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅ ማሻሻያ ተጠናቆ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊቀርብ መሆኑን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡ በረቂቅ አዋጁ ላይ አብዛኛው ለውጥ የተደረገው ባለፈው ወር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ካፀደቀው የባንኮች ለውጭ መከፈት ከፖሊሲ ጋር ለማጣጣም ነው፡፡ የውጭ ባንኮች እንዴት ወደ ኢትዮጵያ ገብተው መሥራት እንደሚችሉ ረቂቅ አዋጁ በዝርዝር ይደነግጋል፡፡

የውጭ ባንኮች እንዲገቡ አራት ተደጓሚ (Subsidiary)፣ ቅርንጫፍ (Branch)፣ የውክልና ቢሮ (Representative Office) እና በሥራ ላይ በሚገኙ የአገር ውስጥ ባንኮች ውስጥ አክሲዮን መግዛት አማራጭ ሆነው ቀርበዋል፡፡ ባንኮቹ ከአራቱ አንዱን አማራጭ ወይም ሁሉንም መጠቀም ይችላሉ ተብሏል፡፡

አንድ የውጭ ባንክ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ባንኮች ውስጥ አክሲዮን መግዛት ከፈለገ የሚፈቀድለት እስከ 30 በመቶ ብቻ ሲሆን የውጭ ዜጋና ባንክ ያልሆነ የውጭ ድርጅት ግን አምስት በመቶ የአገር ውስጥ ባንክ አክሲዮን መግዛት ይችላሉ፡፡ ይህ ማለት አንድ የአገር ውስጥ ባንክ ለውጭ ዜጋ፣ ለውጭ ባንክና ድርጅት መሸጥ የሚችለው ጠቅላላ አክሲዮን ከ40 በመቶ መብለጥ የለበትም፡፡

ቀመሩ የአገር ውስጥ ባንኮች በውጭ ሰዎች እንዳይዋጡና የአገር ውስጥ ባለአክሲዮኖች ዋነኛ ባለድርሻ ሆነው እንዲቀጥሉ ያስችላል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ረቂቅ አዋጁ የውጭ ባንኮች ከአገር ውስጥ ባንኮች አክሲዮን እንዲገዙ ቢፈቅድም እንደ አዋሽና ዳሸን ያሉት አቅም ያላቸው የሀገር ውስጥ ባንኮች ከትንንሾቹ ባንኮች ድርሻ እንዲገዙ አልፈቀደላቸውም።