Get Mystery Box with random crypto!

አሜሪካ በ30 የቻይና የንግድ ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ ጣለች። የዓለም አንደኛ እና ሁለተኛ ልዕለ | Think Abyssinia

አሜሪካ በ30 የቻይና የንግድ ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ ጣለች።

የዓለም አንደኛ እና ሁለተኛ ልዕለ ሀያል የሆኑት ሀገራት የሆኑት አሜሪካ እና ቻይና የንግድ ጦርነት ከጀመሩ ቆይተዋል። ቻይና በወታደራዊ ቴክኖሎጂ በአሜሪካ ላይ የበላይነትን መውሰዷ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን እንዳሳሰበ ሮይተርስ ዘግቧል። በዚህም የተነሳ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የቻይናውን ግዙፉ የሚሞሪ አምራች ኩባንያ የሆነው ያንትዝ ቴክኖሎጂ ኩባንያን ጨምሮ በ30 ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ ጥለዋል።

በተጨማሪ የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ለቻይና ወታደራዊ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የማይክሮ ቺፕስ ምርቶቻቸውን እንዳይሸጡም እገዳ ተጥሎባቸዋል። ቻይና በበኩሏ ማዕቀቡ አሜሪካንንም ይጎዳል ብላለች። ቻይና ከሩሲያ እና ኢራን ጋር ባላት ግንኙነት ደስተኛ ያልሆነችው አሜሪካ በተለይም የሩሲያን ነዳጅ መግዛቷን እንድታቆም በመወትወት ላይም ትገኛለች።

via - Al ain