Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ማስተላለፍ ሊጀምር መሆኑ ተሰማ። የኢት | Think Abyssinia

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ማስተላለፍ ሊጀምር መሆኑ ተሰማ።

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ከዛሬ ጀምሮ ለተመልካቾቹ በመዝናኛ ቻናሉ ተደራሽ የሚያደርግ ይሆናል ተብሏል። ዛሬ ቀን 11 ሰዓት ላይ ማንቸስተር ሲቲ ከ ሳውዝሀምፕተን በኢቲሀድ ስታዲየም የሚደርጉት ጨዋታ በኢቲቪ መዝናኛ ቻናል የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል።

ከፍተኛ ገንዘብ በማውጣት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎችን የማስተላልፍ መብትን የገዛው ኢቢሲ ጨዋታዎቹ እንደ ከዚህ ቀደሙ ለሀገር ውስጥ ተመልካቾች ብቻ በአንቴና ስርጭት ሳይሆን በሳተላይትም የዲሽ ስርጭት እንደሚኖረውም ተረጋግጧል። ከእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ በተጨማሪ የኳታሩ አለም ዋንጫ ሁሉንም ጨዋታዎች በኢቲቪ መዝናኛ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን እንደሚኖራቸው ታውቋል።