Get Mystery Box with random crypto!

ቴሌ ብር ከኬንያው ኤም ፔሳ ጋር የሚያደርገው ፉክክር ቀላል ይሆንለት ይሆን የሳፋሪኮም ኢትዮ | Think Abyssinia

ቴሌ ብር ከኬንያው ኤም ፔሳ ጋር የሚያደርገው ፉክክር ቀላል ይሆንለት ይሆን


የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአገር አቀፍ ደረጃ የኢንተርኔት አገልግሎት ማስጀመሪያ መረሐ ግብር በመስከረም 26 በወዳጅነት አደባባይ አካሂዷል፤ በዚሁ መርሃ ግብር ላይ መንግሥት በቅርቡ የኢትዮጵያ ገበያን ለተቀላቀለው ሳፋሪኮም የሞባይል ገንዘብ ዝውውር አገልግሎት መስጠት የሚችልበትን ፍቃድ ሰጥቷል፡፡ በዚህም ሳፋሪኮም በኬንያ በኤም ፔሳ የገንዘብ አገልግሎት ያገኘውን ስኬት በኢትዮጵያ ለመድገም እንደሚሠራም አስታውቋል።

#ቴሌ_ብር_እና_ኤም_ፔሳ_ንፅፅር

እኤአ በ2007 የተመሰረተው የኬንያው ኤም ፔሳ ከስድስት መቶ ሺህ በላይ አገልግሎቱን የሚሰጡለት ኤጀንቶች አሉት። በዋናነት በኬንያ፣ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ በግብፅ፣ ጋና ፣ ሞዛምቢክ ፣ ሌሴቶ እና ታንዛኒያ የሚንቀሳቀስ ሲሆን ከ51 ሚሊየን በላይ የተመዘገቡ ደንበኞች አሉት። በዓመት እስከ 314 ቢሊየን ዶላር ድረስ የሚጠጋ የገንዘብ ዝውውርም ያደርጋል።

ከተጀመረ አመት ከስድስት ወር ገደማ የሞላው የኢትዮ ቴሌኮም የቴሌ ብር አገልግሎት ደግሞ ከሁለት ወር በፊት ይፋ በሆነ መረጃ ወደ 23 ሚሊዮን የተጠጉ ደንበኞች አሉት። ከተጀመረ አንስቶም ከ34 ነጥብ 1 ቢሊዮን የሚልቅ የገንዘብ ዝውውር አድርጓል።

የግብር፣ የውሃ፣ የኤሌክትሪክ እና መሰል አግልግሎቶችን ከሚሰጡ በርካታ የመንግሥት ተቋማት፣ ከ13 ባንኮች እንዲሁም ከ22 ሺህ የንግድ ተቋማት ጋር የተሳሰረው ቴሌብር  በመላው አገሪቱ ከ79 ሺህ በላይ ወኪሎች አሉት። ቴሌ ብር በኢትዮጵያ ቀዳሚ የሞባይል ገንዘብ ማስተላለፊያ መሆኑ እድል ቢሆንለትም በዘርፉ የካበተ ልምድ ካለው ኤም ፔሳ ጋ የሚኖረው ፉክክር ቀላል አይሆንም ።

አሁን ላይ አጠቃላይ ኢትዮ ቴሌኮም ያሉት ደንበኞች ቁጥር 52 ሚሊዮን ነው። 120 ሚሊየን ከሚገመተው የሀገሪቱ ዜጋ አንፃር አሁንም ለኤም ፔሳ ያልተነካ እድል ከፊቱ አለ። እድሉን ሊሞክርም ይፋዊ ፍቃድ ተሰጥቶታል።

#ስጋት_ወይስ_በረከት

በጉዳዩ ላይ ለባላገሩ ማብራሪያ የሰጡት የምጣኔ ኃብት ባለሞያዎች ሳፋሪኮም የሞባይል ገንዘብ ማስተላለፍ በኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎት መስጠት  እንደሚጀምር ቀድሞም የሚታወቅ በውል ውስጥም የነበረ መሆኑን አንስተው ጉዳዩ ለህዝብ አዲስ ይሁን እንጂ ለመንግሥትም ሆነ ለሳፋሪኮም አዲስ አይደለም ይላሉ፡፡

የመንግሥት ተቋማት ወደ ግል መዛወር እንቅስቃሴ ላይ ተደጋጋሚ አስተያየት በመስጠት የሚታወቁት የምጣኔ ኃብት ባለሞያው አቶ ክቡር ገና ኢትዮ ቴሌኮም የቴሌ ብር አገልግሎት ሥራ ካስጀመረ የአንድ ዓመት ከስድት ወራት እድሜ ብቻ እንዳለው አንስተዋል፡፡

ተቋሙ አዲስ አገልግሎት እንደመጀመሩ መጠን የዳበረ ልምድ እንደሌለው ጠቁመው በዚህ ሁኔታ ላይ የኬንያው ኤምፔሳ ወደ ሥራ መግባቱ ለቴሌ ብር የሕልውና አደጋ ሊሆን እንደሚች ጠቁመዋል፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ለዓመታ የቴሌኮሙን ዘርፍ  በሞናፖሊ (በብቸኝነት) ተቋጣጥሮት የቆየው ኢትዮቴሌኮም የትርፉ ምንጭ ገበያውን ያለ ተወዳደሪ መያዙ እንደሆነ የሚያነሱት አቶ አብዱልመናን መሃመድ  ተቋሙ  ከመንግሥት የጥበቃ  ጫንቃ ወርዶ በእግሩ እንዲቆም ተወዳዳሪ ያስፈልገዋል ባይ ናቸው፡፡

እንደ ኤም ፔሳ ያሉ ተቋማት ተወዳዳሪ ሆነው መምጣታቸው በባንክ የክፍያ ስርዓት ተደራሽ ያልሆነውን ማህበረሰብ  ክፍል ተደራሽ የሚሆንበትን ዕድል እንደሚፈጥር ያነሳሉ፡፡ ኤም ፒ ኤሳ  የውጭ ድርጅም በመሆኑ አብዛበኛውን ትረፉን የሚያሰላው በውጭ ምንዛሬ ነው የሚሉት አቶ ክቡር ገና በበኩላቸው ፤ ኢትዮጵያ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት ከዶላር አንፃር የብር የመግዛት አቅሟን እያዳካመች በመሆኑ እና ተቋሙ  ለሚሰጠው የአገልግሎት ክፍያ  በብር የሚሰበስብ መሆኑ ሊያዋጣው እንደማይችል ያነሳሉ፡፡

ሳፋሪኮም በቴሌኮም አገልግሎት በተጨማሪ የሞባይል ገንዘብ ዝውውር ላይ እንዲገባ  መደረጉ ትልቁን ትርፍ  በዚህ ዘርፍ እንዲያገኝ  ዕድል ሊሰጠው እንደሚችል ጨምረው ጠቁመዋል። ኤም ፔሳ በኬንያ ከ40 በመቶ በላይ ትርፋን የሚያገኘው  በሞባይል ገንዘብ ማስተላለፍ እንደሆነም ይጠቁማሉ ።

አገሪቱ በጦርነት ኢኮኖሚ ላይ ባለችበት፣ ዓለም በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ባልተረጋጋበት ሁኔታ ላይ ተቋማትን ለውጭ ገበያ ማቅረቡ  ከዋጋ አንፃር አዋጭ እንደማይሆን ያነሱት አቶ አብዱልመናን ኤም ፔሳን ከመጋበዙ በፊት የተወሰነ ጊዜ ቢጠበቅ የተሻለ እንደነበረ ተናግረዋል፡፡

ባላገሩ ቴሌቭዥን

  መልካም በዓል
• @ThinkAbyssinia •