Get Mystery Box with random crypto!

በፍራንኮ ቫሉታ ለሚገቡ ዕቃዎች የውጭ ምንዛሪን ምንጭ ማሳወቅ ግዴታ እንዲሆን ተወሰነ። የኢትዮጵ | Think Abyssinia

በፍራንኮ ቫሉታ ለሚገቡ ዕቃዎች የውጭ ምንዛሪን ምንጭ ማሳወቅ ግዴታ እንዲሆን ተወሰነ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በፍራንኮ ቫሉታ አማካይነት ዕቃዎችን ወደ አገር የሚያስገቡ ግለሰቦች፣ የሚጠቀሙበት የውጭ ምንዛሪ የራሳቸው ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ የባንክ ስቴትመንት እንዲያቀርቡ የሚያስገድደውን አሠራር እንደገና መጀመሩን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

ብሔራዊ ባንክ ይህንን ዕርምጃ የወሰደው በፍራንኮ ቫሉታ ዕቃ እናስመጣለን በማለት ከጥቁር ገበያ ዶላር እየገዙ መልሰው በማስወጣት እየሠሩ ያሉ መኖራቸውን ማረጋገጥ በመቻሉ እንደሆነ፣ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡በመሆኑም የጥቁር ገበያ ምንዛሪን ለመቆጣጠር ብሔራዊ ባንክ በፍራንኮ ቫሉታ ተጠቃሚዎች ላይ ያደርግ የነበረውን ቁጥጥር እንደገና ይጀምራል፤›› ያሉት ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዋጋ ንረቱንና ሕገወጥ የውጭ ምንዛሪ ዝውውርን ለመከላከል ከውጭ ወደ አገር የሚገቡ አንዳንድ ምርቶች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ የሚወስን መመርያ በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚሆን ይናገር (ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡ ምርቶቹ መግባታቸው ጥሩ ቢሆንም አሁን ካለው የውጭ ምንዛሪ እጥረትና ከአስፈላጊነታቸው አንፃር ታይቶ፣ አንዳንድ ምርቶችን ከውጭ እንዳይገቡ ክልከላ ይደረግባቸዋል ብለዋል፡፡