Get Mystery Box with random crypto!

አዲሱ የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት በዓመት አምስት ቢሊየን ብር ወጪ ይቀንሳል ተባለ። በተያዘው | Think Abyssinia

አዲሱ የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት በዓመት አምስት ቢሊየን ብር ወጪ ይቀንሳል ተባለ

በተያዘው በጀት ዓመት በ73 ተቋማት እየተተገበረ የሚገኘው የኤሌክትሮኒክ የመንግሥት ግዥ ሥርዓት፣ በዚህ ዓመት ብቻ አምስት ቢሊየን ብር ወጪ ሊቀንስ ይችላል ተብሎ እንደሚጠበቅ የመንግሥት ግዥ ባለሥልጣን አስታወቀ። አዲሱ አሠራር በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት ሙሉ ለሙሉ ሲተገበር፣ የግዥ ወጪን በ50 በመቶ ይቀንሰዋል መባሉን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

በ18 ሚሊየን ብር ወጪ የበለፀገው አዲሱ የግዥ ሥርዓት፣ ባለፈው በጀት ዓመት በዘጠኝ መሥሪያ ቤቶች ላይ በሙከራ ደረጃ ተተግብሮ የነበረ ሲሆን፣ ግዥ ሲከናወን የሚወጡ አላስፈላጊ ወጪዎችን ከመቀነስ ባለፈ፣ ብልሹ አሠራሮችን ለማስቀረት ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል። በአዲሱ ሶፍትዌር ላይ ያልተመዘገቡ አቅራቢዎች፣ የፌዴራል መንግሥት ቢሮዎች በግዥዎች ላይ መሳተፍ እንደማይችሉ ባለሥልጣኑ አስታውቋል፡፡

• @ThinkAbyssinia •