Get Mystery Box with random crypto!

የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከሌሎች ሀገራት ጋር ያለው ንፅፅር የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚ | Think Abyssinia

የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከሌሎች ሀገራት ጋር ያለው ንፅፅር

የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር ትላንት ማምሻውን የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማሻሻያ መደረጉን አስታውቋል። በዚህም መሰረት ቤንዚን በሊትር - ባለፈው ወር ከነበረበት 47 ብር 83 ሳንቲም ወደ 57 ብር ከ05 ሣንቲም ከፍ ብሏል። ይህም ከአፍሪካዊቷ ሀገር አይቮሪኮስት ጋር ያለው የዋጋ ንፃሪ በ20 ሳንቲም ብልጫ አሳይቷል።

እንዲሁም ነጭ ናፍጣ በሊትር - ባለፈው ወር ከነበረበት 49 ብር 02 ሳንቲም ወደ 59 ብር ከ90 ሣንቲም ከፍ ብሏል። ይህም በጎረቤት ኬንያ ካለው ዋጋ የአንድ ብር ከዘጠና ሳንቲም ጭማሪ አሳይቷል። ኬሮሲንም በሊትር ባለፈው ወር ከነበረበት 49 ብር 02 ሳንቲም ወደ 59 ብር ከ90 ሣንቲም ከፍ ማለቱ ተገልጿል። 

ሚኒስትሩ በመግለጫው የአውሮፕላን ነዳጅ፤ ቀላል ጥቁር ናፍጣና ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሥራ ላይ የነበረው ዋጋቸው ባለበት እንዲቀጥል የወሰነ ሲሆን የታለመ ድጎማ ተጠቃሚ የሕዝብ ትራንስፖርት ተሽክርካሪዎች በሚጠቀሙት ነዳጅ ላይ በሁለተኛው ምዕራፍ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አልተደገረም ብሏል።

• @ThinkAbyssinia •