Get Mystery Box with random crypto!

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በአወዳይ እና ጎንደር ከተሞች ጀመረ። ሳፋሪኮ | Think Abyssinia

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በአወዳይ እና ጎንደር ከተሞች ጀመረ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት በአወዳይ እና ጎንደር ከተሞች  ያስጀመረው ይህ የደንበኞች ሙከራ የሳፋሪኮምን ኔትወርክ እየሞከሩ ያሉትን ከተሞች ቁጥር ዐስር የሚያደርሰው ሲሆን፤ ባለፉት አራት ሳምንታት ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሐረማያ፣ ባሕር ዳር፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ሞጆ እና ደብረ ብርሃን ላይ ሙከራው መጀመሩ ይታወቃል፡፡

ኩባንያው እንዳሳወቀው የሁለቱ ከተሞች ደንበኞች በO7 በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መስመር የስልክ ቁጥሮቻቸውን መርጠው ሲም ካርድ መግዛት የሚችሉ ሲሆን፤ ኔትወርኩን ለአንድ ወር ያህል እንዲሞክሩት የሚረዳ የደንበኝነት ማስጀመሪያ የዳታ፣ የድምጽ እና የጽሁፍ መልዕክቶች ጥቅል የያዘ መሆኑም ተገልጿል።

በተጨማሪም ደንበኞች በኔትወርክ ሙከራው ዳታ መጠቀም፣ ጥሪዎች እና የጽሁፍ መልዕክቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ እንደሚችሉም ገልጿል፡፡

• @ThinkAbyssinia •