Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ለሁላችሁም እንደምን ቆያችሁ?እስኪ ለዛሬ ስለ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን አንዳንድ እዉነታ | የካሌብ ጽሑፎች

ሰላም ለሁላችሁም እንደምን ቆያችሁ?እስኪ ለዛሬ ስለ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን አንዳንድ እዉነታዎችን ላካፍላችሁ...መቼም ነገሩ ባህርን በማንኪያ መሆኑ የታወቀ ነው.. መልካም ንባብ ይሁንላችሁ..

( ፩ )አንደኛ

➨ ሞትን ሳይቀምስ ወደ ብሔረ ሕያዋን የተወሰደውና አዕምሮውን መቶ በመቶ(100%) የተጠቀመበት ብቸኛው የምድራችን ሰው #ሔኖክ /ኢትዮጵያዊ/ ነው። እስከዛሬ ድረስ አዕምሮውን ሙሉ በሙሉ የተጠቀመ ምድራዊ ሰው የለም። የሰው ልጅ የአእምሮው ልዕልና የሚለካው በምድራዊ እውቀት ሳይሆን በሰማያዊ ጥበብ ነው። ሰው የአዕምሮው ልዕልና (IQ) ሲያድግ ወደ ቅድስና ደረጃ ይሸጋገራል እንጅ ምዕራባዊያን እንደሚሉት በምድራዊ ጥበብና እውቀት አይመላም። ይሄን ደግሞ ያደረገ ብቸኛው ሰው አባታችን ቅዱስ ሔኖክ የተስፋይቷ ምድር ልጅ ብቻ ነው።

፪ ሁለተኛ

➨ሲዖልም ገነትም የሚገኙት በመላኩ 15 ክንድ ከምድር ከፍ ብለው ኢትዮጵያ (አፋር ኤርታሌ እና ጎጃም ጣና አካባቢ በቅደም ተከተል) ነው ይህን ስንል አለማትን ማለትም ሲዖል የሚባል ራሱን የቻለ አለም ሌላ ሰማይ ላይ እንዳለ ልብ ልትሉ ይገባል ምን አልባት በሚቀጥለው ስለ (፯) ሰባቱ ሰማያት እና (፻) መቶ አለማት የማቀርብላችሁ ከሆነ በይበልጥ ግልጽ የሚሆን ይመስለኛል ። እናም በድሮው ወሎ ክፍለ ሀገር በዛሬው አፋር ውስጥ የሚገኘው #ኤርታሌ የሚባለው ቦታ ግን ነገሩ የራሱ የሆነ ሰማያዊ ምስጢር አለው። እዚህ ቦታ ላይ የሚገኘው እሳተ ገሞራ ወይም የእሳት ባህር #አዛዝኤል የታሰረበት ቦታ መሆኑን አንዳንድ መዛግብት ላይ ለማንበብ ችያለሁ። አዎ ይህ ቦታ የምድራዊው ወይም የኛ ሰማይ ሲኦል መገኛ እንደሆነና ጎጃም የሚባለው ሀገር ላይ በተለይም ደግሞ ጣና ዙሪያ የገነት መገኛ እንደሆኑ አንዳንድ የብራና መዛግብት ይጠቁማሉ።

( ፫ ) ሶስተኛ

➨ በዓለም ትክክለኛነቱ የተረጋገጠለት የዘመን ስሌት ያለው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ (ኢትዮጵያ) ውስጥ ነው። ይህንንም ዓለም ሲመራበትና ምዕራባውያኑ እየተጠቀሙበት ያለው ወይም ደግሞ የማያውያን ካላንደር ትክክል እንዳልሆነ ይህንንም በ መጋቤ ሃዲስ ሮዳስ ታደሰ የቀመር ስሌትና እውቀት በመጠቀም በኢትዮጵያዊያን አቆጣጠር ሰኔ 14/2012/ የታየው የፀሀይ ግርዶሽ ትንተና የዚህን ቀመር እውነታን ፍንትው አድርጎ የገለፀና ታእማኒነቱን ያረጋገጠ ሀቅ ነው፡፡

( ፬ )አራተኛ

➨ በነብያት እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች የተባለች ብቸኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ ነች። አዎ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች። መመኪያዋም አለኝታዋም እርሱ ነውና። ይች ሀገር ከፈጣሪዋ ጋር ልዩ ትስስር ያላት የዓለማችን ብቸኛ ሀገር ነች። ፈጣሪ በስጋ የተመላለሰባት ሀገር እስራኤል እንኳን የኢትዮጵያን ያህል ክብር በፈጣሪ ዘንድ የላትም ይህ ጽንፈኝነት ሳይሆን ሐቅ ነው እውነትን የሚወድ እና የሚፈልግ ቢኖር አስቀድሞ ሁሉን ይመርምር ። ለዚህ ደግሞ ማሳያ የሚሆነን ነገር አለ። እግዚአብሔር በነብያቱ በኩል እስራኤላዊያንን ሲገስጽ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያዊያን ልጆች አይደላችሁም ነበር ያለ። ልብ በሉ! እንደ ኢትዮጵያዊያን!

( ፭ ) አምስተኛ

➨ ታቦተ ጽዮን የሙሴ ጽላት የምትገኝባት ሀገር ኢትዮጵያ ነች። በአምላክ ትዕዛዝና ቀመር የተሰራችው ይህቺ ጽላት በጠቢቡ ሰለሞን የንግሥና ጊዜ የደቡብ ንግስት (ንግስተ አዜብ) ወይም የሳባ ንግስት (ንግስተ ሳባ) ተብላ በምትጠራዋ ንግስት.. በቀዳማዊ ምኒልክ አማካኝነት ነበር ወደ ሀገራችን የገባችው። ምዕራባዊያን ይህቺን መመኪያችንን ጽላት ዘሙሴ ለመውሰድ ብዙ ጊዜ ሞክረዋል። ነገር ግን አልተሳካላቸውም። አይሳካላቸውምም። ምክንያቱም እነርሱን ትታ በእኛ ምድር በሀገራችን ትኖር ዘንድ በእግዚአብሔር ፍቃድ መጥታለችና ሊወስዷት ቢኳትኑም አያገኟትም።

ይህ #የካሌብ_ጽሑፎች_የቴሌግራም_ድህረገጽ ነው

ስለመረጡን አክሮታችን ላቅ ያለ ነው! ይህንን ድህረገጻችንን ያልተቀላቀላችሁ ከታች አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ቀለም ልብ ቅርጽ መሀል ያለውን ሰማያዊ ሊንክን በመንካት #Join ያድርጉ ድህረገጹ አስተማሪ እና ቁምነገር አዘል ሆኖ ካገኙት ሌሎችም ይቀላቀሉን ዘንድ በቅንነት #Share #Forward በማድረግ አብረውን ይቀጥሉ


ለመ ላ ል

@TheHabesha0
@TheHabesha0
@TheHabesha0

እኔ #ዓጼ_ካሌብ ነበርኩ መልካም ምሽት ይሁንላችሁ እያልኩ ለዛሬ ያዘጋጀሁላችሁን ጦማርን በዚሁ አበቃለሁ!

.....................................................